ፊሊፒንስ ተገልጋዮችን ኮስተር ብለው በሚያስተናግዱ የመንግስት ሰራተኞችን በደመወዝ ልትቀጣ ነው
በፊሊፒንስ የመንግስት ሰራተኞች ፈገግ ብለው ካላስተናገዱ የስድስት ወር ደመወዝ ቅጣት ይጠብቃቸዋል
ሀገሪቱ አዲስ ህግ ያወጣችው ሰራተኞች ኮስታራ ናቸው የሚሉ አስተያየቶቸ ከተገልጋዮች በመምጣታቸው ነው
ፊሊፒንስ ኮስተር ብለው በሚያስተናግዱ የመንግስት ሰራተኞች ላይ አዲስ ህግ ማውጣቷ ተሰምቷል
የእስያዋ ሀገር ፊሊፒንሷ ሙላኒ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች ኮስተር ብለው ለተገልጋዮች አገልግሎት እንዳይሰጡ አስጠንቅቃለች፡፡
የከተማዋ ከንቲባ አርስቶትል አጉዌሪ እንዳሉት የመንግስት ሰራተኞች በውስጣቸው ምን አይነት ችግር ቢኖርም ተገልጋዮችን ፈገግ ብለው ተገልጋዮችን እንዲያስተናግዱ አዲስ ህግ አውጥተዋል።
በዚህ ህግ መሰረት ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ኮስተር ብሎ አገልግሎት ፈላጊዎችን ካስተናገደ እስከ ስድስት ወር የሚደርስ ደመወዙን ሊያጣ ይችላል፡፡
ከንቲባው እንዳሉት ረጅም ርቀት ተጉዘው አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ በርካታ ሰዎች ወደ ቢሮ ሲደርሱ በሰራተኞች ፊት ላይ መኮሳተርን እንደሚያዩ እና ይህም አገልግሎት ለማግኘት ያላቸውን ፍላጎት እየጎዳው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የተገልጋዮችን አስተያየት እንደሚሰሙ እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ጥራት እንደሚያሳድጉ ከዚህ በፊት በምርጫ ቅስቀሳ ላይ ቃል የገቡት የአሁኑ ከንቲባም ሰራተኞች ፈገግ ብለው እንዲያስተናግዱ የሚያስገድድ ህግ አውጥተዋል፡፡
ይሁንና አዲስ ህግ በወጣባት በዚች ከተማ ከመኖሪያ ቤቶች ውጪ ባሉ ስፍራዎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ወይም ማስክ ማድረግ ግዴታ ሆኗል፡፡