ከ25 ዓመት በኋላ ወደ ትምህርት ገበታ በመመለስና ውጤት በማምጣት ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ገብታለች
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በነቀምቴ ከተማ በሚገኘው ዋናው ካምፓስ እና በሌሎች ካምፓሶቹ ከትናት ጀምሮ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።
በዛሬው እለት ወደ ዩኒቨርሲቲው በማቅናት ምዝገባ ያካሄደቸው አንዲት አዲስ ተመዝጋቢ እናት ግን የበርካቶችን ቀለብ ስባለች።
ይህች እናት ተማሪ ይመኙሽ ምትኩ የምትባል ሲሆን፤ በ47 ዓመት እድሜዋ ዩኒቨሲቲውን መቀላቀሏ የበርካቶችን ቀልብ ሊስብ መቻሉ ተነግሯል።
የአራት ልጆች እናት የሆነቸው ተማሪ ይመኙሽ ምትኩ ከፍቃዷ ውጪ በቤተሰቦቿ ፍላጎት ትዳር እንድትይዝ በመደረጉ ትምህርቷን ለማቋረጥ ተገዳ እንደነበረ ኤፍ.አይ.ቢ ይዞት በወጣው ዘገባ አመልክቷል።
ትምህርቷን ባቋረጠችበት ወቅት የ10ኛ ክፍል ተማሪ እንደነበረች የምትናገረው ተማሪዋ፤ ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ትምህርቷ በመመለስ መማር መጀመሯን ትናገራለች።
በዚህም በየዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በመውሰድ 360 ነጥብ በማምጣት ወለጋ ዩኒቨርሲቲን መቀላቀል መቻሏን ተናግራለች።
በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ የጤና ትምህርት ለማጥናት በማጥናት በሴቶች እና በህጻናት የጤና ችግሮች ዙሪያ የመስራት ፍላጎት እንዳላት አስታውቃለች።
ወ/ሮ ይመኙሽ ምትኩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኑኑ ቁምባ ወረዳ ትምህርቷን ተከታትላ ማጠናቀቋንም ተናግራለች።
በያዝነው ወር የ69 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ እና የ11 ልጆች አባት የሆኑት ግለሰብ ጅማ ዩኒቨርሲቲን መቀላቀላቸው ይታወሳል።