ራድዮ እና ጂፒኤስን የሚያቋርጥ የጸሀይ ሞገድ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ
ባለሙያው እንዳሉት የመጀመሪያው ስቶርም በፈረንጆቹ ጥር 22 የተከሰተ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ዛሬ ጥር 23 ይከሰታል
የኤንኦኤኤ የስፔስ ዌዘር ፕሪድክሽን ማዕከል እንዳመለከተው እየተከሰተ ያለው የሶላር ስቶርም ኃይል የማቋረጥ 60 በመቶ እድል አለው
ራድዮ እና ጂፒኤስን የሚያቋርጥ 'የሶላር ስቶርም' ወይም የጸሀይ ሞገድ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ።
የራድዮ ሞገድን እና ጂፒኤስን የሚቋርጥ 'የሶላር ስቶርም' ዛሬ ሊከሰት ይችላል ተብሏል።
የሶላር ስቶርም መሬትን ከመታት በኋላ በፖሲፊክ ውቅያኖስ አካባቢ በትናንትናው እለት የራድዮ ሰርጭት ተቋርጧል።
ኧርዝ ዶት ኮም ባወጣው መረጃ መሰረት በትናንትናው እለት በምዕራብ አሜሪካ እና በደቡብ አሜሪካ ጫፍ በ10 ሰአት ከ20 ደቂቃ ወይም በኢኤስቲ ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ50 ደቂቃ ላይ ለአጭር ሰከንዶች የራድዮ ስርጭት መቋረጥ አጋጥሞ ነበር።
የናሽናል ኦሽኒክ ኤንድ አትሞስፌር አድሚኒስትሬሽን (ኤንኦኤኤ) መካከለኛ የሚባል ሶላር ስቶርም መከሰቱን ሪፖርት አድርጓል።
ሶላር ስቶርም ከፍተኛ የኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲየሽን ፍንዳታዎች ሲከሰቱ የሚፈጠር እና ከአንድ ደቂቃ እስከ አንድ ሰአት ሊቆይ የሚችል ነው።
ድንገተኛ የኤሌክትሮማግኔቲክ ፍንዳታ ከብርሃን ፍጥነት በላይ የሚጓዝ ነው።
ሁለቱ ዋልታዎች በከተፍኛ ኢነርጃይዝድ ፖርቲክልስ ስለሚጠቁ እስከ ሰባት ስአት ድረስ የራድዮ ስሬጭት መቋረጥ ሊያጋጥም እንደሚችል ኧርዝ ዶት ኮም ጠቅሷል።
ይህ ሶላር ስቶርም በዚህ አመት በጸሀይ የተለቀቁት ተከታታይ ሶላር ስቶርም አካል ነው ተብሏል።
የኤንኦኤኤ የስፔስ ዌዘር ፕሪድክሽን ማዕከል እንዳመለከተው እየተከሰተ ያለው የሶላር ስቶርም ኃይል የማቋረጥ 60 በመቶ እድል አለው።
የራዲዮ ስርጭት፣ የአቬሽን ግንኙነት እና የሳተላይት ኦፐሬሽን ሊያቋርጥ የሚችል ሌላ ሶላር ስቶርም በዛሬው እለት ሊከሰት እንደሚችል ተገልጿል።
ስለሶላር ስቶርም ጉዳይ በመደበኛነት በኤክስ ገጹ ላይ ፖስት የሚያደርገው የፊዚክስ ባለሙያ ታምታ ስኮቭ "አንድ ወይም ሁለት ሶላር ስቶርም በዛሬው እለት ወደ መሬት እየመጣ ነው" ብሏል።
ባለሙያው እንዳሉት የመጀመሪያው ስቶርም በፈረንጆቹ ጥር 22 የተከሰተ ሲሆን ሁለተኛው እና ከፍተኛው ደግሞ ዛሬ ጥር 23 ይከሰታል።
የኤንኦኤኤ እንደገለጸው ከፍተኛ የሶላር ፍሌር በሚከሰትበት ወቅት ከፍተኛ ግጭት ስለሚፈጠር የራድዮ ሞገዶች ጥንካሬ እንዲያጡ እና ስርጭት እንዲቋረጥ ያደርጋል።