በተሳካ ሁኔታ ጨረቃ ላይ መንኮራኩር ያሳረፈችው ህንድ ሮኬት ወደ ጸሀይ አስወነጨፈች
ህንድ ውሃ ይገኝበታል ወደተባለው የጨረቃ ደቡባዊ ክፍል በሰኬት ማሳረፋ ከፍተኛ ደሰታ ፈጥሮላታል
ህንድ በጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ የጠፈር መንኮራኩር በተሳካ ሁኔታ ካሳረፈች ከ10 ቀናት በኋላ ጸሀይን ለማጥናት 'አድትያ ኤል-1' የተሰኘች መንኮራኩር አስወንጭፋለች
ህንድ በጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ የጠፈር መንኮራኩር በተሳካ ሁኔታ ካሳረፈች ከ10 ቀናት በኋላ ጸሀይን ለማጥናት 'አድትያ ኤል-1' የተሰኘች መንኮራኩር አስወንጭፋለች።
ይህ ለህንድ የመጀመሪያ ጸሀይን የማጥናት ተልዕኮ መሆኑን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
የጠፈር መንኮራኩሯ በከሲሪሃሪኮታ ከሚገኘው የህንድ ምስራቅ ዳርቻ በፖላር ቬሂክል ሮኬት አማካኝነት ከረፋዱ 5:50 ላይ ተወንጭፋለች።
የህንድ የስፔስ ጥናት ድርጅት(አይኤስአርኦ) አድትያ-1 የማስወንጨፉ ሂደት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ብሏል።
ሮኬቱ ሳይተላይቷን በተፈለገው ኦሮቢት ላይ አሳርፏታል ብሏል ድርጅቱ። እንደ ድርጅቱ ከሆነ የመጀመሪያ የህንድ የሶላር ተልዕኮ ሰን-ኧርዝኤል 1 ላይ ለመድረስ ጉዞዋን ጀምራለች።
አድትያ-1 ለአራት ወራት ያህል 1.5 ሚሊዮን ኪሎሜትር ተጉዛ ላግሬንዝ ፖይንት ወይም ኤል 1 በተባለ የኦርቤት ክፍል ራሷን ታስቀምጣለች።
በግራቪቴሽናል ኃይል አማካኝነት ባላንሷን ትጠብቃለች።
አይኤስ አርኦ እንገለጸው አድትያ1 የህንድ ሶላር ሚሽን ከሰፔስ ሆኖ የጸሀይን ከባቢ የሚያጠናበት የመጀመሪያው ተልዕኮ ነው ብሏል።
የጠፈር መንኮራኩሩ ሰባት ክፍሎች ያሉት ሲሆን ይህም ጥልቅ የሆነውን የጸሀይ ክፍል፣ክሮሞስፌር ወይም ከ400ኪ.ሜ እስከ 2100ኪ.ሜ ያለውን የጸሀይ ክፍል እና የላይኛውን የጸይ ክፍል ለመመልከት እና ለማጥናት ያስችላል።
ህንድ ውሃ ይገኝበታል ወደተባለው የጨረቃ ደቡባዊ ክፍል በሰኬት ማሳረፋ ከፍተኛ ደሰታ ፈጥሮላታል።