የአሜሪካው የጠፈር ሳይንስ ተቋም ናሳ በቀጣዮቹ ቀናት ምድር በጸሀይ መብረቅ ልትመታ እንደምትችል አሳስቧል
ከነገ ጀምሮ ለተወሰኑ ቀናት በዓለም ሀገራት ላይ ሬዲዮ ላይሰራ እንደሚል ተገለጸ፡፡
የአሜሪካው የጠፈር ሳይንስ ተቋም ናሳ ባወጣው ማስጠንቀቂያ ከፈረንጆቹ ህዳር 30 ጀምሮ ምድር በጸሀይ መብረቅ ልትመታ እንደምትችል አስጠንቅቋል፡፡
በዚህ የጸሀይ መብረቅ ምክንያትም በደቡባዊ የዓለማችን ሀገራት ሬዲዮ በተለመደው መንገድ ላይሰሩ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ከሬዲዮ በተጨማሪም የጂፒኤስ አገልግሎት ሊቋረጥ ይችላል የተባለ ሲሆን ይህም ከነገ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ የአገልግሎት መቆራረጥ አልያም ሙሉ ለሙሉ አለመስራት ሊያጋጥም ይችላል ተብሏል፡፡
የመሬት ደቡባዊ ክፍል የሚባሉ ሀገራት ሰባት ሲሆኑ ደቡብ አፍሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ፓራጓይ፣ ዩራጋይ፣ ሌሴቶ፣ ናሚቢያ፣ ግሪናዳ እና ዶምኒካ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
የናሳ ማስጠንቀቂያን ተከትሎ ከሁለት ሳምንት በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በምድር ላይ በሚደርስ የጸሀይ መብረቅ ምክንት በዓለም ላይ ኢንተርኔት ይቋረጣል የሚሉ ዜናዎች ሲሰራጩ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይሁንና ናሳ ባወጣው ተጨማሪ መግለጫ በመብረቁ ምክንያት ኢንተርኔት በመላው ዓለም ይቋረጣል በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል፡፡
በመሬት ደቡባዊ ክፍል ባሉ ሀገራት ኢንተርኔትን ጨምሮ ኤሌክትሪክ፣ ጂፒኤስ እና ሬዲዮ አገልግሎቶች ለሰዓታት የመቋረጥ አደጋ እንደሚያጋጥማቸው ይሄው ተቋም አስታውቋል፡፡