በአፍሪካ ብዙ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ህዝብ ያላቸው ሀገራት እነማን ናቸው?
የኢንተርኔት ኢኮኖሚ በአፍሪካ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ወደ 230 ቢሊዮን ዶላር ያድጋል ተብሏል

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ብዛት በአምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች
በአፍሪካ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ዜጎች በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከግማሽ በላይ አሻቅቧል።
ከአንድ ቢሊዮን በላይ ህዝብ ባለባት አፍሪካ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ የኢንተርኔት ኢኮኖሚ መጠን ወደ 230 ቢሊዮን ዶላር ያድጋል ተብሏል።
እንደ አፍሪካ ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘገባ ከሆነ ናይጀሪ ከ109 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ።
በሰሜን አፍሪካዊቷ ግብጽ ደግሞ 75 ሚሊዮን ዜጎቿን ኢንተርኔት በማስጠቀም ሁለተኛዋ የአፍሪካ ሀገር ተብላለች።
ሌላኛዋ ከአፍሪካ የተሻለ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ህዝብ ያላት ሀገር ደቡብ አፍሪካ ስትሆን 41 ሚሊዮን ዜጎቿ አገልግሎቱን ያገኛሉ።
ከጠቅላላ ህዝቧ ውስጥ 84 በመቶው ኢንተርኔት የሚያገኝበት ሀገር የሆነችው ደግሞ ሞሮኮ ስትሆን 32 ሚሊዮን ዜጎች የኢንተርኔት አገልግሎት ይጠቀማሉ ተብላል።
በተያያዘ ከዚህ ቀደም አለም አቀፍ የሞባይል ዳታ ዋጋ ላይ የተደረገ ጥናት 5 ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ኢንተርኔትን በርካሽ ዋጋ ከሚያቅርቡ 50 የዓለም ሀገራ ውስጥ መካተት መቻላቸው ተመላክቷለል።
ከእነዚህም ውስጥ ጋና ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ኢንተርኔትን በርካሽ ዋጋ በማቅረብ ቀዳሚ ስትሆን፤ ኢትዮጵያ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተች ሲሆን፤ ደረጃዋም ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት መካከል ኢንተርኔትን በዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ 10ኛ ከዓለም ደግሞ 73ኛ ላይ ተቀምጣለች።
በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ የ 1 ጊጋ ባይት የኢትነርኔት ዳታ ዋጋ 1 የአሜሪካ ዶላር ወይም 52 ብር ገደማ እንደሆነ ተመላክቷል።