የሶማሌ ክልል የምክርቤት አባል በጅግጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ተገደሉ
በተኩሱ አራት ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል
ግድያውን የፈጸመው በጅግጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ በጥበቃ ስራ ላይ የነበረ ግለሰብ መሆኑን ክልሉ አስታውቋል
የሶማሌ ክልል ም/ቤት አባል የነበሩት ወ/ት ጁዌሪያ መሀመድ ኢብራሂም በጅግጂጋ አውሮፕላን ማረፊያ በተተኮባቸው ጥይት መገደላቸውን የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡
ግድያው የተፈጸመው በዛሬው እለት ከቀኑ 9 ሰአት መሆኑን የገለጸው የክልሉ መንግስት በምክርቤት አባሏ ህይወታቸው ወዲያው ሲያፍ ሌሎች አራት ሰዎች ቆስለው እየታከሙ ነው፡፡
ግድያውን የፈጸመው በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ በጥበቃ ስራ ላይ የነበረ ግለሰብ መሆኑን ክልሉ አስታውቋል፡፡
የክልሉ መንግስት ግድያውን ፈጽሟል የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና በአየርመንገዱ የነበረው ክስተት በቁጥጥር ስር ውሎ ወደ ነበረበት ተመልሷል ብሏል፡፡