ኩዌት በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ሰጠች
እርዳታው የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው ተብሏል
በእርዳታው ወደ 6 ሺህ 500 የሚጠጉ ሰዎች ተጠቃሚ ሆነዋል ተብሏል
ኩዌት በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ሰጠች፡፡
ኩዌት እርዳታው ሰጠችው በኢትዮጵያ በሚገኘው የኩዌት ቀጥታ ተራድኦ ድርጅት አማካኝነት ነው።
እርዳታው የምግብ (ሩዝ፣ዘይትና ደረቅ ወተት )ና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተራድኦ ድርጅቱ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙዘሚል ዑመር አህመድ፤ በ“ዲናን” አከባቢ ብቻ 1 ሺህ 300 አባወራዎች የወከሉ ወደ 6 ሺህ 500 የሚጠጉ ሰዎች የእርዳታው ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል፡፡
በሶማሌ አከባቢ መሰል አስቸኳይ እርዳታ ሲደረግ መጀመሪያ እንዳልሆነ የገለጹት በኢትዮጵያ የ”ዳይሬክት አይድ” ዳይሬክተር ጠሃ ማህሙድ በበኩላቸው፤ ድርጅታቸው ጦርነት የተደረገበትን የሀገሪቱ ሰሜን ክፍል አከባቢን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙትን የተፈጥሮ አደጋዎች የተጋረጡባቸውና በድርቅ የተጎዱ ወገኖች በርካታ እርዳታ ማድረጉን ለ"አል-አይን አል-አክባር" ተናግረዋል።
እንደፈረንጆቹ በ1994 ጽ/ቤቱን በኢትዮጵያ ያቋቋመው የኩዌት ቀጥታ ተራድኦ ድርጅት፤ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከሚሰጠው ሰብዓዊ እርዳታ በተጨማሪ እንደ ትምህርት እና ጤና የመሳሰሉ ዘርፎችን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ያለ ድረጅት መሆኑም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡