ሶማሊያ በፈረንጆቹ 2017 በተከሰተ ፍንዳታ የተገደሉ 587 ሰዎች አሰበች
በሁለቱ የቦንብ ፍንዳታዎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ጋዜጠኞችና የጤና ባለሙያዎች ከተገደሉት መካከል ናቸው
የሶማሊያ መንግስት የፈረንጆቹን ጥቅምት 14፣2017 የጥቃቱ ሰለባዎች የሚታሰቡበት ብሄራዊ የበዓል ቀን አድርጎታል
የሶማሊያ መንግስት የፈረንጆቹን ጥቅምት 14፣2017 የጥቃቱ ሰለባዎች የሚታሰቡበት ብሄራዊ የበዓል ቀን አድርጎታል
አለምአቀፉ ማህበረሰብ በፈረንጆቹ ጥቅምት 2017 በሶማሊያ በተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ የሞቱን 587ሰዎችና የቆሰሉትን 316 ሰዎች ለሚያስቡ ሶማሊያውያን አጋርነቱን አሳይቷል፡፡
ሶማሊያውያን የመንግስት ባለስልጣናትና ህግ አውጭዎችን ጨምሮ እንዲሁም የአፍካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ባለስልጣናት ሶማሊያውያን እንዲረጋጉና አንድነታቸውን አጠናክረው ሰላም እንዲያሰፍኑ ጠይቀዋል፡፡
የሶማሊያው ተመድ ባወጣው መግለጫ ዘግናኝ በሆነው ጥቃት የሞቱትንና የተረፉትን ማሰቡንና ተመድ ለሶማሊያውያን ያለውን አጋርነት አረጋግጦላቸዋል፡፡
በሶማሊያ የተመድ ዋና ጸኃፊ ተወካይ ጀምስ ስዋን በተመድ “ከሶማሊዎች ጋር የተመድ ቤተሰቦች ወደፊቱ ላይ በማተኮር በሰላም፣ በመልካም አስተዳደርና ብልጽግና ያለውን መሻሻል መቀጠል ይገባል“ ብለዋል፡፡
ከ2017 ጥቃት በኋላ በሶማሊያ ያለው መሻሻል ምንም እንኳን የአክራሪ ሃይሎችን ቅጣት ቢቀምሱም ፣ ሶማሊያውያን ቻይና የተሻለ ነገን ፈላጊ መሆናቸውን ያሳያል ብለዋል፡፡ በሁለት ተከታታይ የቦንብ ፍንዳታዎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ጋዜጠኞችና የጤና ባለሙያዎች ይገኙበታል፡፡
የሶማሊያ መንግስት የፈረንጆቹ ጥቅምት 14፣2017 ብሄራዊ የሀዘብን ቀን አድርጎታል፤ የጥቃቱ ሰለባዎች የሚታሰቡበት ቀን ይሆናል፡፡
የጥቃት ሰለባዎችን የማሰቡ ስነስርአት ከፍተኛ የጽጥታ ቁጥጥር ባለበት ወቅት ነው፡፡ ይህ የሆነው የሶማሊያ ብሄራዊ ደህንነት አልሸባብ በወቅቱ ለፈጸመው ጥቃት ጥቅም ላይ ያዋለው ሰልፈሪክ አሲድ ማግኘቱን ተከትሎ ነው፡፡ ደህንነቱ ሰልፈሪክ አሲድ የያዘውን ሰው መያዙን ገልጾ አንዴት ወደ ሀገር እንደገባ እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል፡፡