በኮሮና ዘገባ ምክንያት ሶማሊያ ጋዜጠኞችን እያሰረች ነው
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ፋርማጆ ስልጣን ከያዙ በኋላ 8 ጋዜጠኞች ተገድለዋል ብሏል
በሶማሊያ የኮሮና ቫይረስ/የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ጉዳይ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ ነው ተባለ
በሶማሊያ የኮሮና ቫይረስ/የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ጉዳይ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ ነው ተባለ
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ፋርማጆ ለኮሮና ቫይረስ/ኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሚዲያ ዘገባ አገልግሎት አስፈላጊ ነው ቢሉም እስካሁን በትንሹ አራት ጋዜጠኞች በዘገባቸው ምክንያት ታስረዋል፡፡
በሶማሊያ ከአርብ ጀምሮ ከ80 በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን አምስት ሰዎች ሞተዋል፡፡
ስለቫይረሱ መከላከያ ቁሳቁስ አቅርቦትና ነጋዴዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዴት እቃ እንደሚያስገቡ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ታስረዋል፤ አንዳንዶቹም የጻፉትን ዜና ተገደው እንዲተውት ተደርገዋል፡፡
መቀመጫውን ሎንደን ያደረገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሶማሊያ ለጋዜጠኞች አደገኛ የሆነች ሀገር ነቸ፤ ፕሬዘዳንት ማሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ከአልሸባብና ከመንግስት በሚሰነዘሩ ጥቃቶች በትንሹ ስምንት ጋዜጠኞች ተገድለዋል ብሏል፡፡
ታዛቢዎች የቫይረሱ ወረርሽኝ ተጨማሪ ችግር ይፈጥራል ብለዋል፡፡
የሶማሊያ ጋዜጠኞች ሲንዲኬት ዋና ጸሀፊ አብዳሌ አህመድ ሙሚን “በቅርቡ እያየነው ያለው ነገር በጣም የተለየ ነው” ብሏል፡፡
መንግስት ስለኮድ 19 የሚዘግቡ ጋዜጠኞችን ለማስፈራራት አልሞ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡
መቀመጫውን አሜሪካ ኒዮ ወርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲፒጄ በሶማሊያ ጋዜጠኞች እየታሰሩ መሆኑን አስታቋል፡፡ በጉዳዮ ላይ ቪኦኤ በአሜሪካ የሚገኘውን ሶማሊያ ኢምባስ ምላሽ ጠይቆ መልስ አለማግኘቱን ጽፏል፡፡