የሶማሊያ የምርጫ ጉዳይ አሁንም ድረስ መቋጫ ያላገኘ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል
ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብል ስብሰባውን የጠሩት፤ የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ስልጣን የሚያራዝመው ውሳኔ ቢቀለበስም፤አሁንምድረስ መቋጫ ባላገኘው የምርጫ ጉዳይ መፍትሄ ለማበጀት እንደሆነ ተገልፀዋል፡፡
ስብሰባው በመጪው ግንቦት 20 እንደሚካሄደም ነው የቢቢሲ ዘገባ የሚያመለክተው፡፡
የፑንትላንድን ጁባላንድን ግዛቶች በተጠራው ስብሰባ ያላቸውን አስታየት እንዲሰጡ ይጠበቃል፡፡
በሶማልያ ራስ ገዝ መስተዳደር መሪዎች መካከል ሲካየዱ የቆዩ ውይይቶች ካለ ውጤት መጠናቀቃቸው የሚታስ ነው፡፡
ይህ የሆነበት ምክንያት ፕሬዝዳንት ሞሓመድ ዓብዱላሂ ፋርማጆ ከምርጫ በፊት ከምርጫ መውረድ አለባቸው እንዲሁም መንግሰት ምርጫን በማካሄድ ስኬታማ ልምድ የለውም በሚል ተቃውሞ እንደሆነም ጭምር፡፡
ለዚህም ፕሬዝዳንት ፋርማጆ በምርጫ ዙርያ የሚደረጉትን ውይይቶች በጠቅላይ ሚኒሰትር ሞሃመድ ሁሴን እንዲመሩ ኃላፊነት ሰጥተዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒሰትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብል የተጠራውና በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደው ስብሰባም የሶማልያ መሪዎች በምርጫ ዙርያ በመምከር መፍትሄ ለማበጀት እንደሚያስችላቸው ከወዲሁ ተጠብቀዋል፡፡