አሜሪካ ለሩሲያ ድጋፍ የሚያደርጉ ሀገራት የአሜሪካን ገበያ እንደሚከለከሉ አስጠንቅቃለች
ደቡብ አፍሪካ የጦር መሳሪያ ለሩሲያ ሰጥታለች የሚለው በአሜሪካ መንግስት የቀረበባት ክስ ተቀባይነት የለውም ስትል ተቃውማለች።
አሜሪካ ባለፈው አመት መጨረሻ አካባቢ ማዕቀብ የተጣለባት የሩሲያ መርከብ ከደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከሚገኘው የባህር ኃይል ሰፈር የጦር መሳሪያ ጭና ሄዳለች የሚል ክስ አቅርባለች።
የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት አሜሪካ ባቀረበችው ክስ ላይ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
በደቡብ አፍሪካ የአሜሪካ አምባሳደር ባለፈው ታህሳስ ወር የሩሲያ መርከብ የጦር መሳሪያ ጭና መሄዷን እና ይህም ሀገሪቱ በዩክሬን ጦርነት ካላት የገለልተኝነት አቋም ጋር አብሮ አይሄድም ሲሉ ተናግረዋል።
ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ሩሲያ በዚህ አመት ከደቡብ አፍሪካ ጋር ወታደራዊ ልምምድ ማድረጓ ሁኔታውን በንቃት እንዲከታተሉ ማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል።
ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ አህጉር የሩሲያ ወሳኝ አጋር ተደርጋ የምትታይ ነች።
በትናንትናው እለት የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎዛ ጋር በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ መነጋገራቸው ተገልጿል።
አሜሪካ ለሩሲያ ድጋፍ የሚያደርጉ ሀገራት የአሜሪካን ገበያ እንደሚከለከሉ አስጠንቅቃለች።
ባለፈው ጥሩ ወር የአሜሪካ ገቢዎች ሚኒስትር ጃኔት የለን ደቡብ አፍሪካን ቀጎበኙበት ወቅት አሜሪካ በሩሲያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ የሚጥስ "በፍጥነት እና በከባዱ" ይቀጣል ብለው ነበር።