የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ከስምምነቱ በኋላ “በኢትዮጵያ ሰላም እየመጣ በመሆኑ በጣም ደስተኞች ነን” አሉ
ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ህብርት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀ መንበር መሆኗ ይታወቃል
ሲሪል ራማፎሳ፤ በዴሞክራቲክ ኮንጎ ያለውን ሁኔታ መሻሽሎች እየታዩበት ነው ብለዋል
በመንግስት እና ህወሓት መካከል በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ስምምነተ ተከትሎ በኢትዮጵያ ሰላም እየወረደ በመሆኑ ደስተኞች ነን ሲሉ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ተናገሩ፡፡
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት የአህጉሪቱን ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮንች በተመለከተ ላላፉት ቀናት በአዲስ አባባ ሲካሄድ በቆየው 36ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ነው፡፡
የመንግስትና የህወሓትን የሰላም ስምምነት የሚቆጣጠርና የሚያስከብር የተልዕኮ ቡድን ተቋቋመ
በመንግስትና በህወሓት መካከል የተደረሰው ስምምነት ለኢትዮጵያ ምጣኔሀብት ያለው ተስፋ ምንድነው?
ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ህብርት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀ መንበር መሆኗ ይታወቃል፡፡
በዚህም “የጥይት ድምጽ የማይሰማባት”ን የአፍሪካ አህጉር እውን ለማድረግ እየተደረገ ባለው ጥረት አበረታች የመሪነት ሚና ስትጫወት መቆየቷ ይታወቃል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በጉባኤው ባቀረቡት ሪፖርት እስካሁን ግጭቶችን ለመፍታት ሲደረጉ በቆዩ ጥረቶች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ እንደ ትልቅ ስኬት ካቀረቡት አንዱ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለማቆም የተሄደው ርቀትና በፕሪቶሪያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ነበር፡፡
የፕሪቶሪያው ስምምነት በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎ ኦባሳንጆ፣ በቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ፉምዚል ምላምቦ ንጉካ አሸማጋይነት የተካሄደ ስኬታማ ድርድር እንደነበር አይዘነጋም፡፡
እንደ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አገላለጽ ከሆነ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ለውጥ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡
ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ “በኢትዮጵያ ሰላም እየወረደ በመሆኑ በጣም ደስተኞች ነን”ም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡
በተጨማሪም በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ያለው ግጭትን ለማስቆም ጥረት እየተደረገ መሆኑንና መሻሻሎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡
ሁሉም አካላት ጦርነቱን ለማስቆም ቁርጠኛ መሆናቸው የሚያመላክቱ ሪፖርቶች አሉ ያሉት ሲሪል ራማፎሳ፤ ግጭቱን ለመፍታት የአንጎላ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦም አድንቀዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳዲክ) በሞዛምቢክ የሚሰተዋለውን ግጭትን ለማስቆም እየወሰደ ያለውን እርምጃም የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
ራማፎሳ በሰሜናዊው የአህጉሪቱ ክፍል ስላለው ሁኔታ ሲናገሩም በአራት የሳህል ሀገራት (መፈንቅለ መንግስት በተካሄደባቸው ሀገራት) ያለው ሁኔታ ተረጋግቶ ወደ ሰላም እና ዴሞክራሲ በአስቸኳይ እንዲመለስ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡