በደቡብ አፍሪካ የኮሮና ህክምና የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር 60 በመቶ ጨምሯል ተብሏል
በአፍሪካ ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን ያስመዘገበችው ደቡብ አፍሪካ ከአምስት ወራት በኋላ አዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር መጨመሩን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
በአንድ ቀን ብቻ 13 ሺህ 246 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ይህ አሀዝ ባለፉት አምሰት ወራት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል።
በሆስፒታሎች የኮሮና ቫይረስ ህክምና የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥርም በ60 በመቶ መጨመሩም ተገልጿል።
ባለፉት ስምንት ቀናት ውስጥ በአማካኝ በየዕለቱ 8 ሺህ 436 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ሀገሪቱ በድጋሚ የቫይረሱን ስርጭት መከላከል የሚያስችል አዲስ የእቀባ እርምጃዎችን እንደምትወስድ ገልጻለች።
ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳም የምሽት እንቅስቅሴዎች ላይ እቀባ የጣሉ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ ከተሞች የአልኮል መሸጫ ተቋማት ላይ የሰዓት ገደብ ጥለዋል።
በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሲጠቁ 58 ሺህ 118 ዜጎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።