ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ ነጻ ያወጣው ኤኤንሲ ፓርቲ ጥምር መንግሰት ለመመስረት ሊገደድ ነው
ባለፈው ረቡዕ እለት የተካሄደው ምርጫ በትናንትናው እለት ሲጠናቀቅ ኤኤንሲ 40.19 በመቶ ድምጽ አግኝቷል
ኤኤንሲ የአናሳ ነጮች የበላይነት እንዲያከትም ካደረገው ከ1994 ምርጫ ወዲህ ያሉ ምርጫዎችን በከፍተኛ ድምጽ ሲያሸንፍ ቆይቷል
ደቡብ አፍሪካን ከነጭ አፓርታይድ አጋዛዝ ነጻ ያወጣው ፓርቲ ከአስርት አመታት የበላይነት በኋላ ጥምር መንግስት ለመመስረት ሊገደድ ነው።
በስራ አጥነት፣ በኢትፍትሃዊነት እና በኃል እጥረት ምክንያት የተበሳጩት ደቡብ አፍሪካውያን፣ ሀገሪቱን ከነጭ አፓርታይድ ነጻ ላወጣው የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ(ኤኤንሲ) ድምጻቸውን ነፍገውታል።
የደቡብ አፍሪካው የነጻነት ታጋይ የኔልሰን ሚኔዴላ የሆነው ይህ ፓርቲ በ2019 ካገኘው የ57.5 በመቶ ድምጽ ዝቅ በማለቱ ከተቀናቃኖቹ ጋር ስልጣን ለመጋራት ይገደዳል ማለት ነው።
"ከእያንዳንዱ እና ከማንኛውም ጋር መነጋገር እንችላለን" ያሉት የደቡብ አፍሪካ የማድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከማን ጋር ጥምረት ለመመስረት እንዳሰቡ የተነሳላቸውን ጥያቄ አለመመለሳቸውን ሮይተርስ የደቡብ አፍሪካውን ኤስኤቢሲ ቴሌቪዥን ጠቅሶ ዘግቧል።
ባለፈው ረቡዕ እለት የተካሄደው ምርጫ በትናንትናው እለት ሲጠናቀቅ ኤኤንሲ 40.19 በመቶ ድምጽ አግኝቷል።
ኤኤንሲ የአናሳ ነጮች የበላይነት እንዲያከትም ካደረገው ከ1994 ምርጫ ወዲህ ያሉ ምርጫዎችን በከፍተኛ ድምጽ ሲያሸንፍ ቆይቷል።
ነገርግን ባለፈው አስር አመት ውስጥ በሀገሪቱ የስራ አጥነት በማደጉ፣ ኢኮኖሚው እድገት ባለማሳየቱ እና በኃይል እና በመንገድ መሰረተ ልማቶች ችግር በመፈጠሩ ምክንያት ፓርቲው ሲያገኝ የነበረው ድጋፍ እንዲቀንስ ምክንያት ሆነዋል።
በምርጫው የሀገሪቱ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ዲሞክራቲክ አሊያንስ(ዲኤ) 21.8 በመቶ ድምጽ ያገኘ ሲሆን በጃኮብ ዙማ የሚመራው ኡምክንቶ ዊ ሲዝዊ(ኤምኬ) 14.58 በመቶ ድምጽ ማግኘት ችሏል። በቀድሞው የኤኤንሲ የወጣቶች መሪ የሚመራው ቀኝ ዘመሙ የኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተር(ኢኤፍኤፍ) ፓርቲ ደግሞ 9.5 በመቶ ድምጽ አግኝቷል።
ኤምኬ ከጠበቀው በላይ ጥሩ አፈጻጻም ቢያስመዘግብም፣ ወጤቱን እንደማይቀበለው መበግለጽ ፍርድ ቤት ሄዶ እንደሚከስ ገልጿል።
"ምርጫ ሙሉ በሙሉ እንዲደገም እንፈልጋሉን" ብለዋል የኤምኬ ቃል አቀባይ ንላሙሎ ንድሌላ።
ንድሌላ ኤምኬ የምርጫ ኮሚሽኑ ሲስተም ተጭበርብሯል ብለዋል።
የኢኤፍኤፍ ፓርቲ መሪ ማሌማ ግን የምርጫውን ውጤት መቀበሉን እና በጥምረት ጉዳይ ከድቀሞ ቤቱ ከሆነው ኤኤንሲ ጋር ለመምከር ፍቃደኛ መሆኑን ተናግሯል።