ሶስት የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኮሳት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተገደሉ
የደቡብ አፍረካ ፖሊስ በግድያ ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል
ሶስት የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኮሳት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገደላቸውን የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዛሬው እለት አስታውቃለች
ሶስት የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኮሳት በደቡብ አፍሪካ ተገደሉ።
ሶስት የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኮሳት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚገኘው ገደም ውስጥ በወንጀለኞች መገደላቸውን የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዛሬው እለት አስታውቃለች።
የደቡብ አፍረካ ፖሊስ በግድያ ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።
የቤተክርስቲያኗ ቃል አቀባይ ባወጡት መግለጫ"ሶስቱ መነኮሳት በገዳማችን ውስጥ በወንጀለኞች ግድያ ተፈጽሞባቸዋል" ብለዋል። ቃል አቀባዩ ግድያውን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም።
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ባለስልጣናት በፕሪቶሪያ አቅራቢያ ባለችው ኩሊናን ውስጥ በምትገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጸውን ግድያ እየመረመሩት ይገኛሉ።
የፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ዲማካሶ ኔቩህልዊ እንደተናገሩት የተገደሉት ሶስቱ መነኮሳት በአስከሬናቸው ላይ የተወጉበት ምልክት መገኘቱን እና ከግድያ ያመለጡት አራተኛው ደግሞ በብረት ዘንግ መደብደባቸውን ገልጿል።
"የግድያው አላማ አልታወቀም" ያሉት ቃል አቀባዩ ተጠርጣሪዎች ምንም ነገር ሳይዙ ከቦታው መሰወራቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
ደቡብ አፍሪካ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ ግድያ የሚፈጸምባት እና የታጣቂዎች ዝርፊያ የተለመደ የሆነባት ሀገር ነች።
ቤተክርስቲያኗ ባወጣችው መግለጫ ከተገደሉት መነኮሳት አንደኛቸው የደቡብ አፍሪካ ሀገረስብከት ተወካይ ናቸው።
ቤተክርስቲያኗም በበኩሏ ምርመራ መጀመሯን እና በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙት የግብጽ አምባሳደር ማሳወቋን ገልጻለች።