የአለም ሜትሮሎዲካል ኤጀንሲ ስለመሬት ሙቀት አስደንጋጭ ነገር ይፋ አደረገ
ሪፖርቱ የበካይ ጋዛ እፍግታ ከኢንዱስትሪ አብዮት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ50 በመቶ መጨመሩን ገልጿል
የአለም ሜትሮሎጂካል ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከሆነ በ2022 የበካይ ጋዝ ልቀት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል
የአለም ሜትሮሎዲካል ኤጀንሲ ስለመሬት ሙቀት አስደንጋጭ ነገር ይፋ አደረገ።
የአለም ሜትሮሎጂካል ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከሆነ በ2022 የበካይ ጋዝ ልቀት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ይህ የተመድ ድርጅት ባለፈው አመት ባወጣው ሪፖርቱ የበካይ ጋዛ እፍግታ ከኢንዱስትሪ አብዮት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ50 በመቶ መጨመሩን ገልጿል።
ከ2021 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ የሚቴን እና የኒትሪየስ ኦክሳይድ እፍግታ ከፍተኛ አመታዊ ጭማሪ ማሳየቱንም ጠቅሷል።
"እንደ ከሰል፣ ነዳጅ እና ጋዝ የመሳሰሉት ታዳሽ ያልሆኑ የኃይል ምንጮች የጸሀይን ሙቀት በመሳብ የአለም ሙቀት መጠን እንዲጨምር እና የአየር ለውጥ እንዲከሰት ያደርጋል" ብሏል ሪፖርቱ።
የድርጅቱ ዋና ጸኃፊ ፔትሪ ታላስ የሳይንስ ማህበረሰቡ ከበርካታ አስርት አመታት በፊት ቢያስጠነቅቅም፣ አለም በተሳሳተ አቅጣጫ እየነጎደ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ኃላፊው እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ያለው የበካይ ጋዝ ልቀት በፖሪስ የአየር ንብረት ጉባኤ በምእተ አመቱ መጨረሻ እንዲኖር ከቀመጠው ግብ በብዙ ልዩነት ይቀልጣል።
ውቅያኖስ በሚሞቅበት እና ጨዋማነቱ በሚጨምርበት ጊዜ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ወጭውች ይጨምራሉ ይላሉ ኃላፋው።
ይህን ለውጥ ለመቋቋም ታዳሽ ያልሆኑ የሀይል ምንጮችን መጠቀም መቀነስ እንደሚያስፈልግ ኃላፈው አሳስበዋል።