የደቡብ ባህል ሙዚቀኞች ቡድን የአፍሪካ የባህል ሙዚቃ ውድድር አሸናፊ ሆነ
ናይጄሪያ ባስተናገደችው የአፍሪካ የባህል ሙዚቃ ፌስቲቫል ውድድር የደቡብ ባህል ሙዚቀኞች ቡድን ኢትዮጵያን በመወከል አሸነፈ።
ቡድኑ ኢትዮጵያን በመወከል ማሸነፉን ያስታወቀው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ነው፡፡
የደቡብ ክልል መንግስት የቡድኑን የደርሶመልስ የአየር ቲኬት ሙሉ ወጪ እና የባህል አልባሳት ወጪን ለመሸፈን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በአካልም ጭምር ተገኝተው የባህል ቡድኑን በማበረታታት የጥበብ አጋርነታቸውን ማረጋገጣቸውም ተዘግቧል፡፡
የርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት አክሎም በዚህ አጋጣሚ አሸናፊ ለሆነው የክልሉ የሙዚቀኞች ቡድን በክልሉ መንግስት እና ህዝብ ስም እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።
ምንጭ፡- ኢቢሲ