ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ እና ታንዛንያ በቢሊዮን ዶላሮች ለማበደር መስማማቷ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጉባኤ ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል
የብድር ስምምምት ደቡብ ኮሪያ ወሳኝ ከሆነው የአፍሪካ የማዕድን እና ግዙፉ የኤክስፖርት ገበያ እንድትሳተተፍ የሚያደርገው ትልቅ ስምምነት አካል ነው ተብሏል
ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ እና ታንዛንያ በቢሊዮን ዶላሮች ለማበደር መስማማቷ ተገለጸ።
ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ከእስያዊቷ ደቡብ ኮሪያ ጋር በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ብድር ለማግኘት መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ይህ የብድር ስምምምት ደቡብ ኮሪያ ወሳኝ ከሆነው የአፍሪካ የማዕድን እና ግዙፉ የኤክስፖርት ገበያ እንድትሳተፍ የሚያደርገው ትልቅ ስምምነት አካል ነው።
ደቡብ ኮሪያ በዚህ ሳምንት ባዘጋጀችው የደቡብ ኮሪያ- አፍሪካ ጉባኤ ላይ ከ30 በላይ የሀገራት መሪዎችን እየስተናገደች ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የፋይንስ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ያሉበት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን አስከትለው ወደ ደቡብ ኮሪያ በማቅናት በጉባኤው ላይ እየተካፈሉ መሆናቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል።
ታንዛንያ በቀጣይ አምስት አመታት ውስጥ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ከደቡብ ኮሪያ በብድር መልክ እንደምታገኝ ገልጻለች። ታንዛንያ በምላሹ ኮሪያን ከሀገሪቱ የውቅያኖስ እና ማዕድን ሀብት ተጠቃሚ ሊያደርጋት የሚችል ሁለት ስምምነቶችን ተፈራርማለች ተብሏል።
በኢትዮጵያ እና በኮሪያ መሪዎችን ውይይት ከተደረገ በኋላ ለአራት አመታት የሚተገበር የ1 ቢሊዮን ዶላር የልማት ፋይናንስ ትብብር መፈረሙን አቢሲ የፋይናንስ ሚኒሰትሩ አቶ አህመድን ጠቅሶ ዘግቧል።
ዘገበው ገንዘቡ እንዴት እንደሚለቀቅ እና ምን ላይ እንደሚውል አልጠቀሰም።
ከባለፈው አርብ እለት ጀምሮ የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ይኦል ከሴራሊዮን፣ ከታንዛንያ እና ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር በተናጠል የተወያዩ ሲሆን ከሌሎች በርካታ መሪዎችም ጋር በተናጠል ይወያያሉ ተብሏል።