መንግስታት ብድራቸውን ለማቃለል የሚዘይዱት ዘዴ ኢኮኖሚውን እንዳያቀዘቅዘው ተሰግቷል
ከፍተኛ ብድር ያለባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን ለማነቃቃት እና አገልግሎቶችን ለዜጎቻቸው ለመስጠት በሚል ብድር ከሀገር ውስጥ እና ከአበዳሪ ተቋማት እና ሀገራት ይወስዳሉ፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ፎረም ሪፖርት ከሆነ የዓለማችን ሀገራት አጠቃላይ ብድር 88 ትሪሊዮን ደርሷል፡፡
አሜሪካ 33 ትሪሊዮን ዶላር በመበደር ቀዳሚ ስትሆን ጃፓን እና ቻይናም ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
እንደ ኢኮኖሚክ ፎረም ሪፖርት ከሆነ መንግስታት ያለባቸውን ብድር ለማቃለል ሲሉ የግብር ህጋቸውን ሊሻሽሉ ይችላሉ የተባለ ሲሆን ይህም ኢኮኖሚውን እንዳይጎዳው ተሰግቷል፡፡