ደቡብ ኮሪያ በእስር ላይ ለነበሩት የቀድሞ ፕሬዘዳንት ፓርክ ጉን ሂይ ይቅርታ አደረገች
የቀድሞዋ ፕሬዘዳንት በስልጣን ላይ እያሉ በሙስና ተጠርጥረው ነበር የታሰሩት
ከፈረንጆቹ 2017 ዓመት ጀምሮ በእስር ላይ የነበሩት ፓርክ 22 ዓመት ተፈርዶባቸው ነበር
ደቡብ ኮሪያ በእስር ላይ ለነበሩት የቀድሞ ፕሬዘዳንት ፓርክ ጉን ሂዬ ይቅርታ ማድረጓን አስታወቀች፡፡
የደቡብ ኮሪያ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ፓርክ ጉን ሂይ በልዩ የይቅርታ አሰራር ከእስር እንዲለቀቁ መወሰኑን የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት (ዮናፕ) ዘግቧል፡፡
የቀድሞዋ ፕሬዘዳንት ለእስር የተዳረጉት በስልጣን ላይ እያሉ በሙስና ተጠርጥረው የ22 ዓመት እስር ተፈርዶባቸው ነው፡፡የደቡብ ኮሪያ መንግስት ይሄንን ውሳኔ የወሰነው የሀገሪቱን ብሄራዊ አንድነት ለማስጠበቅ መሆኑን ገልጿል፡፡
የ69 ዓመቷ ፓርክ ከፈረንጆቹ 2017 ዓመት አንስቶ በእስር ላይ የነበሩ ሲሆን የደቡብ ኮሪያ መንግስት እሳቸውን ጨምሮ ከ3 ሺህ በላይ እስረኞችን ከእስር መልቀቁን አስታውቋል፡፡
የቀድሞዋ ፕሬዘዳንት ከእስር መለቀቀቅ የፊታችን መጋቢት ለሚካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አወንታዊ ሚና ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ያሉ መራጮች የፓርክ ደጋፊዎች የደቡብ ኮሪያ ገዢ ፓርቲን በመቃወም ይታወቃሉ፡፡
የደቡብ ኮሪያ መንግስት ከፓርክ በፊት የደቡብ ኮሪያ ፕሬዘዳንት የነበሩት እና በሙስና ተከሰው የ17 ዓመት እስር ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙት ሊ ሚዩንግ ባክ በምህረቱ አላካተተም፡፡
የደቡብ ኮሪያ ፍትህ ሚኒስትር እንዳሉት በእስር ላይ የሚገኙ ታራሚዎችን ከእስር ለመልቀቅ የጤና ሁኔታ እና የሀገሪቱን ህዝብ አንድነት ማስጠበቅ ዋነኛ መስፈርቶች ናቸው ብሏል፡፡
ከእስር እንዲፈቱ ይቅርታ የተደረገላቸው የቀድሞወ ፕሬዘዳንት ፓር ጉን ሂይ ለተደረገላቸው ድጋፍ የወቅቱ ፕሬዘዳንት ሙን ጃኢንን አመስግነዋል፡፡
የቀድሞወ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዘዳንት ፓር ጉን ሂይ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ግንቦት 2008 ዓ.ም ኢትዮጵያን የጎበኙ ሲሆን ከ10 በላይ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራርመው መመለሳቸወቅ ይታወሳል፡፡