ሁለቱ ኮሪያዎች፤ ዛሬ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የሚሳዔል ሙከራዎችን አደረጉ
ፒዮንግያንግ ከሰሞኑ አዲስ ያበለጸግሁት ነው ያለችውን ተመዝግዛጊ ሚሳዔል ማስወንጨፏን የሚታወስ ነው
ደቡብ ኮሪያ ዛሬ የመጀመሪያውን የባህር ውስጥ የባልስቲክ ሚሳዔል ሙከራ ማድረጓን አስታውቃለች
ሰሜን ኮሪያ እና ደቡብ ኮሪያ ዛሬ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የባልስቲክ ሚሳዔል ሙከራዎችን አደረጉ፡፡
የፕሬዝዳንት ሙንጃዔ ዒን ጽህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ደቡብ ኮሪያ ዛሬ የመጀመሪያ የባህር ውስጥ የባልስቲክ ሚሳዔል ሙከራ ማድረጓን አስታውቋል፡፡
3 ሺ ቶን ክብደት ካላት ባህር ሰርጓጅ ተወንጭፎ የተሞከረው ሚሳዔል ሊቃጡ የሚችሉ ስጋቶችን ለመመከትና የቀጣናው ሰላም ለማስጠበቅ ያግዛል ብሏል ጽህፈት ቤቱ፡፡
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ቀደም ብላ ሁለት የአጭር ርቀት ሚሳዔሎችን አስወንጭፋለች እንደ ኮሪያን ታይምስ ዘገባ፡፡
የባህር ውስጥ ሙከራውም ይህንኑ ተከትሎ የተደረገ ነው፡፡
ፒዮንግያንግ ከሰሞኑ አዲስ ያበለጸግሁት ነው ያለችውን ተመዝግዛጊ ሚሳዔል ማስወንጨፏን ማስታወቋ የሚታወስ ነው፡፡
ይህ በ6 ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነ ነው፡፡ ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሆኑ ወዲህ የተደረገ የመጀመሪያ ሙከራ ነውም ተብሏል፡፡
ጎረቤታሞቹን ባላንጣዎች በማስማማት የኮሪያ ባህረ ገብ መሬትን ሰላም ለማስጠበቅ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በአሜሪካ ጭምር ጥረቶች ተደርገዋል፡፡
የሁለቱ ሃገራት መሪዎች፤ የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተገኙበት፤ በሲንጋፑር ተገናኝተው ቅራኔያቸውን ለመፍታት ተስማምተው እንደነበርም ይታወሳል፡፡