የሰሜን ኮሪያና የደቡብ ኮሪያ የፊኛ እና የድምጽ ማውጊያ ፕሮፖጋንዳ ድራማ ዙሪያ እስካሁን የምናውቀው?
ደቡብ ኮሪያ ግዙፍ ድምጽ ማውጊያዎችን ድንበር ላይ በመትከል ወደ ሰሜን ኮሪያ ፕሮፖጋንዳ ማሰራጨት ጀምራች
ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያ ፐሮፖጋንዳ ማሰራጨቷ ካላቆመች ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን መላኳን እንደምትቀጥል ዝታለች
የሰሜን ኮሪያ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ መላኳን ተከትሎ ደቡብ ኮሪያ ትላልቅ የድምጽ ማውጊያዎችን ድንበር ላይ በመትከል ፕሮፖጋዳዎችን ማሰረጫት ጀምራለች።
ሰሜን ኮሪያ አቋርጣ የነበረውን ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን በትናንትናው እለት ዳግም ወደ ደቡብ ኮሪያ መላክ መጀመሯ ይታወቃል።
ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎች የተላኩባት ደቡብ ኮሪያ በሰሜን ኮሪያ ላይ “የማትቋቋመው” እርምጃዎችን እንደምትወስድ የዛተች ሲሆን፣ ይህም ወደ ሰሜን አቅጣጫ በተዘጋጁት ግዙፍ የድምፅ ማጉያዎች የፕሮፓጋንዳ ስርጭቶችን ያካተተ ነው።
ይህንን ተከትሎም የደቡብ ኮሪያ ጦር ትናንት ከሰዓት ላይ ወደ ሰሜን ኮሪያ አቅጣጫ አዙሮ በተከላቸው ግዙፍ ድምጽ ማውጊያዎች የፕሮፖጋዳ ስርጭት አድርጓል።
ደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ አዙራ በተከለቻቸው ድምጽ ማውጊያዎችም በኪም አስተዳደር የተከለከሉ ዓለም አቀፍ ዜናዎች እና ኬ ፖፕ ሙዚቃዎችን አሰራጭታለች።
ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት የሆኑት ኪም ዮ ጆንግ የድምጽ ማውጊያ የፕሮፖጋዳ ስርጭቱን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ፤ ሴዑል ጠብ አጫሪ ድርጊቷን የማታቆም ከሆን ፒዮንግያንግ እርምጃዎችን መውሰዷን እንደትምቀጥል ዝተተዋል።
ኪም ዮ ጆንግ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎም ሰሜን ኮሪያ ተጨማሪ ቆሻሻ የያዙ 300 ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ መላኳም ነው የተነገረው።
አሁን ላይ የተላኩ ቆሻሻዎች ጥቅም ላይ የዋሉ የመጸዳጃ ቤት ወረቀቶች እና ፕላስቲኮች ብቻ መሆናቸውን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል።
ከጠዋቱ 2:30 በኋላ በሰማይ ላይ የሚንሳፈፍ ቆሻሻ ያዘ ፊኛ እንደማይታይም ነው የደቡብ ኮሪያ ጦር ያስታወቀው።
የሁለቱ ኮሪያዎች የፊኛ ድራማ እንዴት ጀመረ?
የሰሜን ኮሪያ ቆሻሻ ያዙ ፊኛዎቹ ወደ ሴኡል መላክ የጀመረችው የደቡብ ኮሪያ አክቲቪስቶች የፀረ ሰሜን ኮሪያ በራሪ ወረቀት የያዙ ፊኛዎች መላካቸውን ተከትሎ እንደሆነ ይታወቃል።
ሰሜን ኮሪያ ለደቡብ ኮሪያ ምላሽ በፈረንጆቹ ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ በጣም አጸያፊ ቆሻሻዎችን ያዙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፊኛዎችን መላኳም ይታወሳል።
ሰሜን ኮሪያ በፈረንጆቹ ሰኔ 2 ላይ ወደ ደቡብ ኮሪያ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን መላኳን በጊዜያዊነት ማቆሟን አስታውቃ የነበረ ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ የተላከው 15 ቶን ቆሻሻ ለተላከባት የፕሮፖጋዳ ፊኛ በቂ መልስ ይሆናል ብላ ስለምታምን እንደሆነም አስታውቃ ነበር።
ይሁን እንጂ ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ኮሪያ የሚገኝ የማህበረሰብ አንቂ ቡድን ወደ ሰሜን ኮሪያ ሙዚቃዎች፣ ዶላርና በራሪ ወረቀቶችን የያዙ ፊኛዎችን መላኩ ይታወሳል።
ለሰሜን ኮሪያ ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ቡድን፥ 200 ሺህ በራሪ ወረቀቶችን፣ 5 ሺህ የደቡብ ኮሪያ ኬ-ፖፕ ሙዚቃና ድራማዎች የተጫኑባቸው ፍላሾች እንዲሁም 2 ሺህ የባለ 1 ዶላር ኖቶች በ10 ፊኛዎች ከድንበር ከተማዋ ፖቺዮን ወደ ሰሜን ኮሪያ ልኳል።
ይህንን ተከትሎም ሰሜን ኮሪያ በትናትናው እለት ወደ ደቡብ ኮሪያ ቆሻሻ ያዙ ፊኛዎችን ዳግም መላክ እንድትጀምር እንዳደረጋት ነው የተነገረው።
ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ 15 ቶን የሚመዝኑ ቆሻሻዎችን በ3 ሺህ 500 ፊኛዎች ወደ ደቡብ ኮሪያ መላኳ ይታወሳል።