የደቡብ ኮሪያ ፍርድ ቤት የፕሬዝደንት ዩንን እስር እንዲያራዝም የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ
ፕሬዝደንቱ ከስልጣን ተነስተው ለእስር የተዳረጉት ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ባወጁት ለአጭር ጊዜ የቆየ ወታደራዊ አዋጁ ምክንያት ነው
የዩን ጠበቆች ሲአይኦ በዩን ላይ ምርመራ የመክፈት ስልጣን የለውም የሚል መከራከሪያ ሀሳብ በተደጋጋሚ እያቀረቡ ነው
የደቡብ ኮሪያ ፍርድ ቤት የፕሬዝደንት ዩንን እስር እንዲያራዝም የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ።
የደቡብ ኮሪያ ፍርድ ቤት የፕሬዝደንት ዩንን የእስር ቆይታ እንዲያራዝም በአቃቤ ህግ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፕሬዝደንቱ ከስልጣን ተነስተው ለእስር የተዳረጉት ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ባወጁት ለአጭር ጊዜ የቆየ ወታደራዊ አዋጁ ምክንያት ነው።
በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የሙስና ወንጀል ምርመራ የሚያካሂደው ቢሮ (ሲአይኦ) ምርመራውን እየመራ ሲሆን ባለፈው ሀሙስ እለት ጉዳዩን ለአቃቤ ህግ ቢሮ አስተላልፎ ዩንን ግጭት በመቀስቀስና ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ክስ እንዲመሰርትበት ጠይቋል።
ዩን ባለፈው ታህሳስ 14፣2024 ከስልጣን ተነስትው በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን መርማሪዎች ለአጭር ጊዜ በቆየው ወታደራዊ አዋጅ ዙርያ ምርመራ እያካሄዱባቸው ይገኛሉ።
የዩን እስር ጥር 28፣2025 እንደሚጠናቀቅ የገለጸው ሲአይኦ መደበኛ ክስ ከመመስረቱ በፊት አቃቤ ህግ የዩን እስር ለተጨማሪ 10 ቀናት እንዲያራዝም ፍርድ ቤቱን እንደሚጠይቅ ጠብቆ ነበር።
ነገርግን የሴኡል ማዕከላዊ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት "በቂ ምክንያት የለም" በማለት የአቃቤ ህግ ቢሮን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።
የዩን ጠበቆች ሲአይኦ በዩን ላይ ምርመራ የመክፈት ስልጣን የለውም የሚል መከራከሪያ ሀሳብ በተደጋጋሚ እያቀረቡ ነው።
ጠበቆቹ አክለውም በዩን ላይ ሊከፈት የሚችል ማንኛውም የወንጀል ምርመራ የሚካሄደው የከስልጣን የታገዱበትን ጉዳይ እየመረመረ ያለው ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከሰጠ በኋሃ ነው ብለዋል።
የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በበጎ የተቀበሉት ጠበቃው ሲአይኦ ምርመራ ህገወጥ መሆኑንና አቃቤህግ ምርመራውን በድጋሚ እንዲጀምር ጠይቀዋል።