ደቡብ ሱዳን በጥቂት ቀናት ውስጥ በሱዳን በኩል ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ልትጀምር መሆኑን ገለጸች
ሀገሪቱ በሱዳን በኩል ነዳጅ ወደ ውጭ ለመላክ የወሰነችው በሱዳን ጦርነት የፈነዳው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መጠገኑን ተከትሎ ነው
ደቡብ ሱዳን በየቀኑ ከ100-150ሺ በርሜል ነዳጅ ኤክስፖርት እንዲደረግ ወደ ሱዳን ስትልክ ቆይታለች
ደቡብ ሱዳን በጥቂት ቀናት ውስጥ በሱዳን በኩል ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ልትጀምር መሆኑን ገለጸች።
ደቡብ ሱዳን በጥቂት ቀናት ውስጥ ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ልትጀምር መሆኑን ሮይተርስ የደቡብ ሱዳን ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
ሀገሪቱ በሱዳን በኩል ነዳጅ ወደ ውጭ ለመላክ የወሰነችው በሱዳን ጦርነት የፈነዳው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መጠገኑን ተከትሎ ነው።
በሱዳን፣ በሱዳን ጦር እና በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል ጦርነት የተቀሰቀሰው ባለፈው አመት ሚያዝያ ወር ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ እና ረሀብ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል።
በሱዳን በኩል የሚተላለፈው ነዳጅ ለደቡብ ሱዳን 90 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ገቢዋን የሚሸፍን ሲሆን ሱዳን ደግሞ ያስተላለፈችበትን ወይም የትራንዚት ክፍያ ትቆርጣለች። በቅርቡ ወደ ፖርት ሱዳን ያመራውን የደቡብ ሱዳን ልኡክ የመሩት ጋትሉዋክ ማኒሜ ባለስልጣናት ማስተላለፊያ ቱቦው በሚገኝባቸው ቦታዎች ያሉትን የማምረቻ ቦታዎች መጎብኘታቸውን ተናግረዋል።
"ሁሉንም ቱቦዎች ተመልክተናል። የተወሰኑት ደርቀዋል፤ ነገርገን በሙቅ ውሃ እና በኬሚካል እንዲጸዱ ተደርገዋል። አሁን ላይ ቱቦዎቹ ከደቡብ ሱዳን ነዳጅ ለማስተላለፍ ዝግጁ ናቸው"ብለዋል ማኒሜ።
ማኒሜ አክለው እንደገለጹት በጥቂት ቀናት ውስጥ ነዳጅ የማስተላለፍ ሰራውን ለመጀመር የሚያስችል እቅድ ለማውጣት የደቡብ ሱዳን የኢነርጂ ሚኒስቴር ባለስልጣናት የሱዳን መሀንዲሶች ቡድንን ይቀበላሉ። ደቡብ ሱዳን በየቀኑ ከ100-150ሺ በርሜል ነዳጅ ኤክስፖርት እንዲደረግ ወደ ሱዳን ስትልክ ቆይታለች።
ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ የቱቦው ብልሽት የአካባቢ ብክለት እና የምግብ እጥረት አስከትሏል።