“ክፍያችንን በመክፈል ወደ ሕብረቱ አባልነት እንመለሳለን”-ደቡብ ሱዳን
ጁባ ከህብረቱ የታገደችው መክፈል ያለባትን 9 ሚሊዮን ዶላር ባመክፈሏ መሆኑን ህብረቱ አስታውቋል
ለህብረቱ ማዋጣት ያለባትን መዋጮ በላመክፈሏ ከአባልነት የታገደችው ደቡብ ሱዳን መዋጮየን እከፍላለሁ ብላለች
ለህብረቱ ማዋጣት ያለባትን መዋጮ በላመክፈሏ ከአባልነት የታገደችው ደቡብ ሱዳን መዋጮየን እከፍላለሁ ብላለች
ደቡብ ሱዳን አባል ለሆነችበት የአፍሪካ ሕብረት መክፈል ያለባትን ዓመታዊ መዋጮ አለመክፈሏን ተከትሎ መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው አህጉራዊው ተቋም ሀገሪቱን ከሕብረቱ አባልነት መሰረዙን አስታውቋል፡፡
ጁባ ለሕብረቱ ያልከፈለችው ከ 9 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዕዳ እንዳለባት ተገልጿል፡፡
የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ዓርብ የደቡብ ሱዳንን ከአፍሪካ ሕብረት መታገድ ማረጋጡን ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ኤምባሲም ጉዳዩን ለሀገሪቱ መንግስት ማሳወቁን ለአል ዐይን ኒውስ አረጋግጠዋል፡፡
ምክትል አምባሳደር ዴቪድ ደንግ ኮንግ ከከአል ዐይን ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት ይህ ነገር አዲስ እንዳልሆነና ከፍያ ባለመፈጸማቸው እንደተፈጠረ ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ይህንኑ ለሀገራቸው መንግስት ማሳወቃቸውንና ክፍያውን ለመክፈል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ዲፕሎማቱ እንዳሉት ደቡብ ሱዳን ገንዘቡን ያልከፈለችው ባለፉት ጊዜያት በጦርነት ላይ በመቆየቷ እና ብዙ ቅድሚያ የምትሰጣቸው ጉዳዮች ስለነበሩባት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሁሉም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት መዋጮ ይከፍላሉ ያሉት አምባሳደር ዴቪድ ደንግ ኮንግ አሁን የደቡብ ሱዳን መንግስት ገንዘቡን ለአፍሪካ ሕብረት ለመክፈል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ”ገንዘቡን ነገ ብንከፍል በቀጣይ ቀናት ወደ አባልነታችን እንመለሳን” የሚሉት ምክትል አምባሳደሩ በሚቀጥለው ሳምንት ሁሉም ነገር እንደሚስተካከል ተናግረዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን እንደ አውሮፓውያኑ ሐምሌ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ነው የአፍሪካ ህብረት 54 ኛ አባል የሆነችው፡፡ሕብረቱ ከ2 ዓመት በፊት ባወጣው መመሪያ ፣ ከውጭ ሀገራት እና ተቋማት ተጽዕኖ ለመላቀቅ በሚል ማንኛውም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገር የተጣለበትን ዓመታዊ ክፍያ እንዲከፍል እና ይህ ካልሆነ ከአባልነት እንዲታገድ ወስኖ ነበር፡፡