"ጫማየን የምሰቅልበት ጊዜ መድረሱ አሳዝኖኟል።" ብሏል ፋብሪጋስ በትዊተር ገጹ
የቀድሞ የስፔን አማካኝ ተጨዋች ሴስክ ፋብሪጋስ አሰልጣን ለመሆን ጫማ መስቀሉን ገለጸ።
የቀድሞ የስፔን ብሄራዊ ቡድን፣ የአርሰናል፣ የባርሴሎና እና የቸልሲ አማካኝ ተጨዋች የነበረው ሴስክ ፋብሪጋስ ጫማውን በመስቀል አንጸባራቂ የነበረው የ20 አመት የጨዋታ ዘመኑን ዘግቷል።
ፋብሪጋስ ጫማ የሰቀለው በኮሞ አሰልጣኝ ለመሆን ነው ብሏል።
ፋብሪጋስ ተዋቂነት ያተረፈው በ16አመቱ ከባርሴሎና ተዛውሮ ለአርሰናል በተጫወተበት ወቅት ነበር። ፋብራጋዝ የፈረንሳዩን አማካኝ ተጫዋች ፖትሪክ ቬራን በመተካት ተጫውቶ ከፕሪሜር ሊጉ አንዱ ምርጥ ተጨዋች ለመሆን ችሎ ነበር።
በፈረንጆቹ 2005፣ የኤፍኤ ካፕ ያገኘበትን ስምንት የጨዋታ ጊዜያትን(ሲዝን) ካሳለፈ በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ ባርሴሎና በማቅናት ስድሰትት ዋንጫዎችን አንስቷል።
ፋብሪጋስ ከባርሴሎና እናደገና ወደ እንግሊዙ ቸልሲ ክለብ በመቀላቀል ለእሱ ሁለተኛ የሆነውን ኤፍኤካፕ እና ሁለት የፕሪሜር ሊግ ሽልማቶችን ማግኘት ችሎ ነበር።
ነገርግን ትልቁ ስኬቱ ሀገሩ ሰፔን በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የአለም ዋንጫ ውድድር ከኔዘርላንድስ ጋር በነበራት የፍጻሜ ጨዋታ በጭማሪ ደቂቃ በገባችው የማሸነፊያ ጎል ላይ የነበረው ሚና ነው።
"ጫማየን የምሰቅልበት ጊዜ መድረሱ አሳዝኖኟል።" ብሏል ፋብሪጋስ በትዊተር ገጹ።
የአለምዋንጫን ከማንሳት ጀምሮ በአውሮፖ ባደረገው ጨዋታ ሁሉንም አይነት ውድድሮችን ማሸነፉ ትልቅ የስኬት ጉዞ እንደነበረው ገልጿል።
የፋብሪጋስ የመጨረሻ ጊዜውን ያሳለፈው በጣሊያን ሴሪኤ በሁለተኛ ደረጃ በሚገኘው ኮሞ ነው። ፋብሪጋዝ በዚህ ክለብ የአሰልጣኝነት ዘመኑን እንድ ብሎ እንደማጀምርም ተገልጿል።