አንድን ሀገር ለሰባት ሰዓታት ያለመብራት ያቆየው ዝንጆሮ
በስሪላንካ የዝንጆሮ መንጋ በሀይል መስመር ላይ ባደረሰው ጉዳት በመላው ሀገሪቱ ሀይል ለሰዓታት ተቋርጧል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/10/258-191230-whatsapp-image-2025-02-10-at-4.55.27-pm_700x400.jpeg)
በደቡብ እስያ የምትገኘው እስያ 22 ሚሊዮን ህዝብ ባለቤት ናት
አንድን ሀገር ለሰባት ሰዓታት ያለመብራት ያቆየው ዝንጆሮ
በእስያዊቷ ስሪላንካ በትናንትናው ዕለት ለሰባት ሰዓታት ሀይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡
የሀይል መቋረጡን ተከትሎ የሀገሪቱ ዜጎች ቅር መሰኘታቸውን በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹም ቆይተዋል፡፡
የስሪላንካ ሀይል ሚኒስትር ኩማራ ጃኮዲ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሀይል የተቋረጠው ዝንጆሮዎች ባደረሱት ጉዳት ነው ብለዋል፡፡
ጉዳዩ ከስሪላንካም ባለፈ በመላው ዓለም ትኩረት የሳበ ሲሆን ዝንጆሮዎች በሀገሪቱ ዋና የሀይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ጉዳት እንዳደረሱ ተገልጿል፡፡
ጉዳቱን ለመጠገን ሰባት ሰዓታት እንደፈጀ የተገለጸ ሲሆን በተለይም የሕክምና እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በሚል ጥገኛው በልዩ ትኩረት ሲደረግ ነበር ተብሏል፡፡
ዝንጆሮዎች በሄል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ጉዳት ማድረሳቸው የጠለመደ ቢሆንም የአሁኑ አይነት ጉዳት ሲያደርሱ ግን የመጀመሪያው እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ስሪላንካ ከዚህ በፊት ከድንጋይ ከሰል እና ነዳጅ ሀይል ስታገኝ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከውሃ ሀይል ማመንጫ የሚገኝ ሀይል ዋነኛ አማራጭ ሆኗል፡፡
22 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት የደቡብ እስያዋ ስሪላንካ አብዛኛው ህዝቧ በድህነት ውስጥ የሚኖር እንደሆነ የዓለም ባንክ መረጃ ያስረዳል፡፡