የስሪላንካ ፖሊስ በአምባሳደሩ ሞት ዙሪያ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል
በስሪላንካ የፈረንሳይ አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ሞተው ተገኙ፡፡
አምባሳደር ጂን ፓክቴት በፈረንጆቹ ጥቅምት 2022 ላይ ነበር በስሪላንካ እና ማልዴቪስ ፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው ወደ ኮሎምቦ የተጓዙት፡፡
የ53 ዓመቱ ዲፕሎማት በመኖሪያ ቤታቸው ህይወታቸው አልፎ እንደተገኘ ሲጂቲኤን የስሪላንካ ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ አምባሳደሩ ህይወታቸው ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረ የተገለጸ ሲሆን ተጨማሪ ምርመራዎች በመካሄድ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
በፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ለረጅም ጊዜ በውጭ ሀገራት የሚካሄዱ የፈረንሳይ ቋንቋ እና ባህል ማስፋፋት ላይ ሲሰሩ የቆዩ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማት ነበሩ ተብሏል፡፡
ፈረንሳይ የፕሬዝዳንት ፑቲን የቀድሞ ሚስት ንብረትን አገደች
ከዚህ በተጨማሪም በግሎባል ሄልዝ ተቋም ውስጥ የፈረንሳይ ተወካይ፣ በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት ወይም ኔቶ የፈረንሳይ ተወካይ እና በአሜሪካ የፈረንሳይ ኢምባሲ ውስጥ በተለያዩ ሀላፊነቶች ላይ እንደሰሩ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ቃል አቀባይነትን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ሀገራቸውን አገልግለዋልም ተብሏል፡፡