የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች
ቀጣይነት ያለው የሸቀጦች እና የአገልግሎቶች ዋጋ በሚጨምርበት ወቅት የሚከሰተው የኑሮ ውድነት ለኢኮኖሚ ፈታኝ ነው
መንግስት እና ማእከላዊ ባንክ በጋራ በሚያወጧቸው ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ኢኮኖሚውን ማረጋጋት ይቻላል
ቀጣይነት ያለው የሸቀጦች እና የአገልግሎቶች ዋጋ በሚጨምርበት ወቅት የሚከሰተው የኑሮ ውድነት ለኢኮኖሚ ፈታኝ ነው።
ነገሮግን የማይፈታ ችግር አይደለም። መንግስት እና ማእከላዊ ባንክ በጋራ በሚያወጧቸው ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ኢኮኖሚውን ማረጋጋት ይቻላል።
ይህ ጹሀፍ የኑው ውድነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስትራቴጅዎችን ይዘረዝራል።
1. ሞናተሪ ፖሊሲ
የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ አንዱና ቁልፉ ዘዴ የሞናተሪ ፖሊሲ ነው። ማዕከላዊ ባንክ የወለድ መጠንን በማስተካከል የገንዘብ ፍሰትን መቆጣጠር ይችላል።
የወለድ መጠን በሚጨምርበት ጊዜ የብድር መጠን ስለሚቀንስ የሰዎች የወጭ መጠን እና ፍላጎት በዚያው ልክ ይቀንሳል።
2 የፊስካል እርምጃ
መንግስት የፊስካል ፖሊሲ እርምጃን መከል ይችላል። የፊዚካል ፖሊሲ መንግስት ራሱ በሚያወጣው ወጭ ላይ ቀጥጥር እንዲያደርግ እና በሀገሪቱ ያለውን ጠቅላላ ፍላጎት ለመቀነስ የግብር መጠን የሚጨምርበት አሰራር ነው። መንግስት ወጭውን ሲቆጥብ የኑሮ ውድነት እንዲቀንስ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
3. ሰፕላይ ሳይድ ኢንተርቬንሽን
የቀሸጦችን እና አገልግሎቶችን መጨመር ኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ሌላኛው ዘዴ ነው። መንግስት ምርት እንዲጨምር አላስፈላጊ የሆኑ የቀጥጥር ስራዎችን እንዲቀሩ ያደርጋል።
4. የገንዘብ ምንዛሬ ጠንን መቆጣጠር
የኑሮ ውድነትን ለመዋጋት የገንዘብ ምንዛሬ መጠንን መቆጣጠር ወሳኝ ነው። የተረጋጋ የገንዘብ ምንዛሬ በሚኖርበት ጊዜ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ የተረጋጋ ይሆናል፣ ድንገተኛ ከሆነ የዋጋ ጭማሪ ሸማቾችን ይታደጋል።
5. የዋጋ ቀጥጥር
በተወሰኑ ሁኔታውች፣በቀጥታ በገበያው ውስጥ በመግባት የዋጋ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። መንግስት ፈጣን የሆነ የሸቀጦች ዋጋ መናርን ለመከላከል ጣልቃ ይገባል። ነገርግን ይህ እርምጃ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ ነው።
6. ብድርን መቀነስ
የፋይናንስ ተቋማት የሚያበድሩትን እንዲቀንሱ ማድረግ። ይህ በተፈጥሮ ሰዎች ብዙ ወጭ እንዳያደርጉ የሚያስገድድ ሰለሚሆን የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
7. ተወዳዳሪ ገበያ መፍጠር
የገበያ ተወዳዳሪነት መኖር ሰዎች ሸቀጦችን በቅናሽ ዋጋ የሚያገኙበት እድል ይፈጠራል። ጤናማ የሆነ ውድድር በሚኖርበት ጊዜ በቅናሽ የመሸጥ ዝንባሌ ይኖራል።
8. ግልጽነት መፍጠር
መንግስት እና ብሄራዊ ባንክ በኑሮ ውድነት ጉዳይ የሚያራምደውን ፖሊሲ ህዝብ እንዲያውቀው ማድረግ። ግለሰቦች እና ድርጅቶች፣ መንግስት የኑሮ ውድነት ችግርን ይፈታዋል ብለዉ የሚያምኑ ከሆነ ገበያው ይረጋጋል።
በአጠቃላይ መንግስት እነዚህን ዘዴዎች በማጣመር የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር እና ገበያውን ማረጋጋት ይችላል።