ደሃ ሀገራት በእርዳታ ላይ የሚኖራቸው ጥገኝነት የሚያስከትለው ችግር ምንድነው?
ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ወደ ደሃ ሀገራት የሚገባ ከሆነ መንግስታት የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዳያደርጉ እና አማራጭ ገቢ የሚያስገኙ አማራጭ ፖሊሲዎችን እንዳያወጡ ያደርጋል
አስቸኳይ እረዳታ እና ብድር ጠቃሚ ቢሆንም በብድር ላይ የሚኖር ከፍተኛ ጥገኝነት የተለያዩ አሉታዊ ውጤቶችን ያስከትላል
የፋይናንስ ድጋፍ ለዓለም ደሃ ሀገራት እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል። አስቸኳይ እረዳታ እና ብድር ጠቃሚ ቢሆንም በብድር ላይ የሚኖር ከፍተኛ ጥገኝነት የተለያዩ አሉታዊ ውጤቶችን ያስከትላል።
ይህ ጹሁፍ የገንዘብ ድጋፍ ጥገኛ መሆን በዓለም ደሃ ሀገራት ላይ የሚያስከትለውን ዘርፈብዙ የኢኮኖሚ ችግሮችን ይተነትናል።
የኢኮኖሚ አለማደግ እና ጥገኝነት
ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ወደ ደሃ ሀገራት የሚገባ ከሆነ መንግስታት የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዳያደርጉ እና አማራጭ ገቢ የሚያስገኙ አማራጭ ፖሊሲዎችን እንዳያወጡ ያደርጋል።
ደካማ ኢንዱስትሪዎች
ከፍተኛ ብድር የሚኖር ከሆነ ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ትኩረት አይሰጣቸውም። በዚህም ምክንያት የውጭ ሸቀጦች በከፍተኛ መጠን ስለሚጎርፉ የሀገርውስጥ ኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪነት ይጎዳል።
ተጠያቂነትን እና አስተዳደርን ማዳከም
በተወሰነ መልኩ እርዳታ በሀገር ውስጥ የሚኖረውን የተጠያቂነት አሰራር ያዳክመዋል። መንግስታት በውጭ እርዳታ ላይ ጥገኛ በሚሆኑበት ጊዜ ለዜጎች ጥያቄ መልስ ለመስጠት ያቅማማሉ፣ብክነት እና ሙስናም ይፈጠራል።
ለውጭ የኢኮኖሚ መዘባት ተጋላጭነት
በብድር ላይ ጥገኛ የሚሆኑ ሀገራት በውጭ በሚኖረው የኢኮኖሚ መዋዠቅ ይጎዳሉ። በእርዳታ ክፍፍል መቀያየር ወይንም ለጋሾች ፖሊሲያቸውን በሚቀይሩበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ድቀት ይከሰታል።
የእዳ ክምር እና መልሶ የመክፈል ችግር
ምንምእንኳን እርዳታ በስጦታ መልክ ወይም በብድር የሚሰጥ ቢሆንም የብድር ክምር አደጋ አለው። ብክነት ወይም የኢኮኖሚ ድቀት ሲኖር ብድር ለመክፈል አስቸጋሪ ስለሚሆን የብዳር ቀውስን ያስከትላል።
ብድር ላይ ጥገኛ መሆን ለጋሽ ሀገራት ሉአላዊነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ጫና ሊያሳድሩ ይችላሉ። በአጠቃላይ ብድር አስቸኳይ ችግሮችን ለማቃለል አስፈላጊ ቢሆንም ከፍተኛ ጥገኝነት ግን ለተለያዩ ውስብስብ ችግሮች ይዳርጋል። በብድር እና በዘላቂ እድገት መካከል ያለውን ምጥነት መጠበቅ፣ ጠንካራ አስተዳደር እና ተጠያቂነት ለደሀ ሀገራት ዘላቂ ብልጽግና ወሳኝ ነው።