የንግድ አለመመጣጠን የሚያስከትለው ችግር ምንድነው?
የንግድ አለመመጣጠን የሚከሰተው አንድ ሀገር በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ከውጭ የምታስገባው ወደ ውጭ ከምትልከው መጠን ሲያንስ ነው
የንግድ አለመመጣጠን ደንበኞች ምርጫቸው እንዲሰፋ እና ለኢኮኖሚ እድገት አስፈላጊ የሆነ የውጭ ኢንቨስትመን እንዲመጣ ያደርጋል
የንግድ አለመመጣጠን ምን ማለት ነው፤ የሚያስከትለው ችግርስ ምንድነው።
ይህ ጹሁፍ የንግድ አለመመጣጠን ምን እንደሆነ እና ስለሚያመጣው ችግር ይዳስሳል።
የንግድ አለመመጣጠን ትርጉም
የንግድ አለመመጣጠን የሚከሰተው አንድ ሀገር በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ከውጭ የምታስገባው ወደ ውጭ ከምትልከው መጠን ሲያንስ ነው። በአጭሩ ለማስቀመጥ አንድ ሀገር የምትገዛው ሸቀጥና አገልግሎት ከምትሸጠው ካነሰ የንግድ አለመመጣጠን (ትሬድ ዴፍሲት) አጋጥሟታል ማለት ነው።
የንግድ መመጣጠን ማለት ለውጭ ገበያ በሚላከው እና ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገባው ሸቀጥና አገልግሎት መካከል ያለው ልዩነት ነው።
የንግድ አለመመጣጠን እንዴት ይከሰታል?
በርካታ ምክንያት ለንግድ አለመመጣጠን መንስኤ ይሆናሉ።
አንደኛው ምክንያት የደንበኞች ምርጫ ነው። ደንበኞች የውጭ ምርቶችን የሚፈልጉ ከሆነ ለንግድ አለመመጣጠን የራሱ ድርሻ ይኖረዋል።
ሁለኛው ምክንያት ደግሞ የኢኮኖሚ እድገት ነው። በፍጥነት የሚያድግ ኢኮኖሚ ጥሬ እቃዎችን እና ምርቶችን ከውጭ ስለሚያስገባ ለአለመመጣጠን ምክንያት ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪም የምንዛሬ መዋዠቅ፣ መንግስት በታሪፍ እና ኮታ ላይ የሚኖረው ፖሊሲ እና የንግድ ስምምነት በንግድ መመጣጠን ላይ ተጽእኖ ያሳድራል።
የንግድ አለመመጣጠን ሁል ጊዜ አሉታ አይደለም።
የንግድ አለመመጣጠን ደንበኞች ምርጫቸው እንዲሰፋ እና ለኢኮኖሚ እድገት አስፈላጊ የሆነ የውጭ ኢንቨስትመን እንዲመጣ ያደርጋል።
አንድ ሀገር ያጋጠማት የንግድ አለመመጣጠን ችግር በሚፈጥርበት ጊዜ የገንዘብ ምንዛሬን በማረጋጋት፣ የሀገር ውስጥ የንግድ ድርጅቶች ገበያቸውን እንዲያስፋፉ እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የሚተኩ ምርቶችን እንዲያመርቱ በማድረግ የንግድ አለመመጣጠን ማስተካከል ይቻላል።