ሪሚታንስ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚፈጥራቸው እድሎች እና ፈተናዎች
በሪሚታንሰ ላይ የሚኖር ከፍተኛ ጥገኝነት ዜጎች ያሉባቸው ሀገራት የፖሊሲ ለውጥ በሚያደርጉት ጊዜ ተቀባይ ሀገራት ለኢኮኖሚ መናጋት ይዳረጋሉ
በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ወደ ትውልድ ሀገራቸው የሚልኩት ገንዘብ ወይም ሪሚታንስ በተለይም በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ኢኮኖሚ የደም ስር ነው
በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ወደ ትውልድ ሀገራቸው የሚልኩት ገንዘብ ወይም ሪሚታንስ በተለይም በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ኢኮኖሚ የደም ስር ነው። ይህ የረጅም ጊዜ አንደምታ ያለው እና የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተጽእኖ የሚያሳድር ነው።
ይህ ጹሁፍ ሪሚታንስ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ላይ ስለሚኖረው ተጽእኖ፣ እድሎች እና ፈተናዎች ላይ ያተኩራል።
የኢኮኖሚ መረጋጋት እና የድህነት ቅነሳ
የሪሚታንስ ዋነኛ አስተዋጽኦ በተቀባይ ሀገራት ላይ የኢኮኖሚ መረጋጋት ማምጣት ነው። ሪሚታንስ እንደአስተማማኝ የገቢ ምንጭ በማገልገል በእርዳታ ላይ የሚኖረውን ጥገኝነት በመቀነስ ኢኮኖሚውን ያረጋጋል። ከዚህ በተጨማሪም ለተቸገሩ ቤተሰቦች የሚደርሰው ሪሚታንስ ለድህነት ቅነሳ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
የኑሮ ደረጃ መሻሻል
ሪሚታንስ በተቀባይ ሀገራት ዜጎች የኑሮ ደረጃ መሻሻል ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ይኖረዋል። ቤተሰቦች የተሻለ የጤና አገልግሎት፣ ትምህርት እና ቤት እንዲቻገኙ ያስችላቸዋል። ገንዘቡ ወደ ሀገርውስጥ ኢኮኖሚው ውስጥ ሲገባ አጠቃላይ የሆነ የኢኮኖሚ መነቃቃትን ያስከትላል።
ትምህርት እና የክህሎት እድገት
ሪሚታንስ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ለለውጥ መሰረት የሆነው የትምህርት ዘረፍ እንዲቀየር ወይም እንዲሻሻል ሚናውን ይጫዋታል። ብዙ ቤተሰቦች በሪሚታንስ የሚያገኙትን ገንዘብ በልጆች ትምህርት ላይ ስለሚያውሉት የሚፈጥር የተማረ የሰው ሀይል ለማፍራት ያስችላል። ይህም የሀገራቱ ኢኮኖሚ ዘርፈ ብዙ እንዲሆን ይረዳል።
ሪሚታንስ ወደ ስራ ፈጠራ ለመሰማራት የሚያስችል መነሻ ገቢም ይሆናል።
የሪሚታንስ ችግሮች
የሪሚታንስ ጥቅሙ የሚያመዝን ቢሆንም ችግሮችም አሉት። በሪሚታንሰ ላይ የሚኖር ከፍተኛ ጥገኝነት ዜጎች ያሉባቸው ሀገራት የፖሊሲ ለውጥ በሚያደርጉት ጊዜ ተቀባይ ሀገራት ለኢኮኖሚ መናጋት ይዳረጋሉ። ስለዚህ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ክትትል ያስፈልገዋል።