የደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች በፈተና ምክንያት የሀገሪቱን መንግስት ከሰሱ
ተማሪዎቹ ለፈተና የተሰጠው ሰዓት ከማለቁ 90 ሰከንድ በፊት እንድናቆም ተደርገናል በሚል መንግስት ከሰዋል
የደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች ለደረሰባቸው ጉዳት የሚሊየን ዶላር ካሳ ጠይቀዋል
የደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች መምህራችው ለፈተና የተሰጠው ሰዓት ሳያልቅ እንድናቆም አድርጎናል በሚል የሀገሪቱን መንግስት መክሰሳቸው ተገለጸ።
ለፈተና የተሰጠው ሰዓት ከማለቁ 90 ሰከንድ በፊት እንድናቆም ተደርገናል ያሉት ተማሪዎቹ ለዚህም በሚሊየን ዶላረ ካሳ መጠየቃቸውን ተነግሯል።
“ሱኔንግ” የሚል መጠሪያ ያለው የደቡብ ኮሪያ የኮሌጅ መግቢያ ፈተና፣ በጣም ረጅም ሰዓት የሚፈጅና እና ከባድ እንደሆነ የሚነገርለት ሲሆን፤ የፈተናው ውጤንትም ህይወትን የሚቀይር ነው።
8 ሰዓት የሚፈጀው ሴሱንግ ብሄራዊ ፈተና ከኮሌጅ መግቢያነት በዘለለም ለተማሪዎች ለወደፊት የስራ ህይወት እና የፍቅር ግንኙነት ህወታቸው ላይም አስተዋጽ ኦለው የተባለ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት ተማሪዎች፣ ቤተሰቦቻቸው እና የሀገሪቱ መንግስት ለፈተናው ትልቅ ስፍራ ይሰጣሉ።
በዚህ 8 ሰዓት በሚወስደው ፈተና ወቅት የደቡብ ኮሪያ መንግስት የአየር ክልሉን የሚዘጋና የስቶክ ገበያዎችንም መከፍፈቻም እንዲዘገዩ የሚያደርግ ሲሆን፤ ይህም ተማሪዎች በፈተናቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ለማገዝ የሚደረግ ነው።
ታዲያ ከሰሞኑ ሴሱንግ ብሄራዊ ፈተና በመፈተን ላይ የነበረ መምህር ለፈተናው የተሰጠው ሰዓት ከማለቁ ከ90 ሰከንድ በፊት እንዲያቆሙ ማድረጉ ጉዳዩን ወደ ህግ እንዲያመራ አድርጎታል።
ጉዳዩ የተፈጠረው በሴዑል በሚገኝ የተፈና ጣቢያ ሲሆን፤ 90 ሰከንድ እየቀረው ደውል ተደውሎ ፈታኝ መምህር የመልስ ወረቀት ከማሪዎች ላይ መሰብሰብ የጀመረ ሲሆን፤ ተማሪዎችም ተቃውሞዋቸውን በማሰማት ላይ ነበሩ ተብሏል። በኋለ ላይም ችግሩ ተለይቶ ከምሳ እረፍት በኋላ ለተማሪዎች 90 ሰክንድ ጭማሪ የተሰጠ ሲሆን፤ በዚህ ጊዜ ግን ባዶ የተወቱን የመለስ መስጫ ብቻ እንዲሉ ነው የፈቀደላቸው ተብሏል።
ከሰዓት ጋር የተፈጠረው ችግር በተወሰኑ ታሪዎች ዘንድ ጭንቀትን የፈጠረ ሲሆን፤ በቀሪ ፈተና ላይ ማተኮር ያልቻሉ ተማሪዎች የመፈተኛ ጣያውን ለቀው እስከመውጣት ደርሰዋል ነው የተባለው።
ይህንን ተከትሎም ባሳለፍነው ማከሰኞ 39 ተማሪዎች የሀገሪቱ መንግስት ላይ ለደረሰባቸው ኪሳራ የ20 ሚሊየን የደቡብ ኮሪያ ዎን ካሳ እንዲከፍላቸው ክስ የመሰረቱ ሲሆን፤ ይህም ለፈተናው ለመዘጋጀት ያወጡትን ወጪ የሚያካከስ ነው ብለዋል።
የተማሪዎቹ ጠበቃ ኪም ዉ ሱክ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የትምህርት ባለስልጣናት እስካሁን ይቅርታ አልጠየቁም፤ አሁን የመሰረቱት ክስም ውጤታማ እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።
በፈረንጆቹ 2021 ላይ ተመሳሳይ ከስተት አጋጥሞ ነበር የተባለ ሲሆን፤ ይህም ለሴሱንግ ብሄራዊ ፈተና የተሰጠው ሰዓት 2 ደቂቃ እየቀረው ተማሪዎች ፈተና እንዲያቆሙ ተደርጎ ነበር።
ይህንን ተከትሎም ተማሪዎቹ በመሰረቱት ክስ ፍርድ ቤት የ7 ሚሊየን የደቡብ ኮሪያ ዎን ካሳ እንዲከፈላቸው ውሳኔ ማሳለፉም ይታወሳል።