የሞሮኮ ቡድን ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ እድሉን ያለመለመው በአውስትራሊያ ፐርዝ ኮሎምቢያን 1ለ0 በማሸነፋ ነው
በዘንድሮው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ያተጠበቁ አሸናፊዎች፣ ተሸናፊዎችን አስደንግጠዋል።
የጃማይካ ቡድን የእግር ኳስ ኃያሏን ብራዚልን እንድትቀር በማድረግ 32 ቡድኖች በተሳተፉበትን የአለም ዋንጫ ወደ 16ቱ ውስጥ መግባቷ ግርምትን ፈጥሯል።
ይህ የሬጌ ሴቶች በውድድሩ ሳይጠበቁ ድል ቀንቷቸዋል ተብሏል።
ከብራዚል ጋር አቻ በመውጣቱ ወደ ቀጣዩ ዘር ማለፍ ያስደሰታቸው የጃማይካ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሎርኔ ዶናልድሰን ድል መቀዳጀታቸው አስገርሟቸዋል።
በውድድሩ የመጀያዎቹ ሁለት ሳምንታት ሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኖርዎይ እና ተባባሪ አዘጋጇ ከፍተኛ አሸናፊዎች መሆናቸው የዘንድሮውን ውድድር ያልተጠበቀ አድርጎታል ተብሏል።
ጀርመን፣ ብራዚል፣ ካናዳ ተባባሪ አዘጋጇ ኒውዝላንድ እና ቻይኔ ድል ያቀናቸው ብሄራዊ ቡድኖች ናቸው።
በእግርኳስ ደረጃዋ 72 ኛ ላይ ያለችው ሞሮኮ ከውድድሩ ቀድማ እንደምትወጣ ብትገመትም በመጀመሪያ ጨዋታዋ ካስተናገደችው 6 ለ 0 ሽንፈት በኋላ ድል አስመዝግባለች።
የሞሮኮ ቡድን፣ ደቡብ ኮሪያ ጀርመንን የምታሸንፍ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው ዙር የማለፍ እድል ይኖራታል።
የሞሮኮ ቡድን ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ እድሉን ያለመለመው በአውስትራሊያ ፐርዝ ኮሎምቢያን 1ለ0 በማሸነፋ ነው።