የቤጃ ጎሳዎች ምክር ቤት ለካርቱሙ ማዕከላዊ መንግስት የሰጠው እውቅና ማንሳቱ ይፋ አድርጓል
በምስራቅ ሱዳን የሚገኘው የቤጃ ጎሳዎች ምክር ቤት የራስን እድል በራስ ለመወሰን በሚል ጊዜያዊ መንግስት ለመመስረት መወሰኑን እና በካርቱም ለሚገኘውን ማዕከላዊ መንግስት የሰጠውን አውቅና ማንሳቱን አስታውቋል።
“የቤጃ ጎሳዎች ምክር ቤት የፖለቲካ ሴክሬታሪያት” እየተባለ የሚጠራው ድርጅት የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲነቃቃ መወሰኑን ተናግሯል፡፡
የራስ አስተዳደር ተቋማትን እና ወታደራዊ ሃይሎችን የማቋቋም መብት አለኝ ሲለም ተደምጧል ምክር ቤቱ፡፡
በተጨማሪም "የቤጃ ጎሳዎች ምክር ቤት የፖለቲካ ኮሚቴ" የጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛውን ስልጣን ባለቤት መሆኑ ይፋ አድርጓል፡፡
የምክር ቤቱ ውሳኔ ወደ መገንጠል የሚወስድ እርምጃ ነው ተብሎለታል፡፡
የሃዳንዳዋ ጎሳዎች መሪ በሆኑት በአል-አሚን ቱርክ የሚመራው "የቤጃ ጎሳዎች ምክረ ቤት" በቀይ ባህር ግዛት አከበቢ በምስራቅ ሱዳን እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ምክር ቤቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ጥያቄዎችን እያነሳ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ጥያቄዎቹም በየካቲት 2020 በተፈረመው የጁባ ስምምነት መሰረት ከእነዚህም መካከል የቀይ ባህር አስተዳዳሪ ከስልጣን እንዲሰናበቱ ፣የክልሉ ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል መጀመር እና የመሬት ማጸደቂያው እንዲታገድ የሚሉ ናቸው፡፡
እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ የቤጃ ምክር ቤት ደጋፊዎች በምስራቅ ሱዳን የሚገኙ ወሳኝ ወደቦችን እና በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ግዛቱን ከተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ጋር የሚያገናኙ መንገዶችን መዝጋታቸውም ታውቋል፡፡