የሱዳን ጦር፤ የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ በወታደሮቼ ላይ ጥቃት ሰንዝሯል ሲል ከሰሰ
የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ ሱሰዳን ጦር ክስ ከሃቅ የራቀ ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል
ጦሩ የአስ ፒኤልኤም ጥቃት በ2019 የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት የጣሰ ነው ብለዋል
የሱዳን ጦር የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ (ኤስ ፒኤልኤም-ኤን) ወደ ላጋዋ ላይ ሞርታር በመተኮሱ በወታደሮቼ ላይ ጥቃት አድርሷል ሲል ከሷል።
በጥቃቱ ሁለት ፈጣን ደጋፊ ሃይሎች አባላት ቆስለዋል ያለው የሱዳን ጦር፤ የተከሰተው ነገር የተኩስ አቁም ስምምነቱን የጣሰ በመሆኑ የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ተግባሩን እንደሚቀጥል አሳስቧል።
ጦሩ "ኤስፒኤልኤም ካርዶችን በማደባለቅ እና በክልሉ ውስጥ ያሉ ማናቸውንም ማህበራዊ አካላትን ለማደናቀፍ የሚያደረገውን ማንኛውንም ጥረት መግታት በሚያችልና የሁሉም ማህበራዊ ደህንነትን እና ሰላምን በሚያስጠብቅ መልኩ እንሰራለን" ብሏል፡፡
የሱዳን ጦር ይህን ይበል እንጅ የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ (-ኤስ ፒኤልኤም-ኤን) ክሱ ውድቅ እንዳደረገው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ኤስ ፒኤልኤም ቀደም ሲል ሚሴሪያ የተባለው የሚሊሻ ቡድን በሱዳን ጦር ፈጣን ደጋፊ ሃይሎ ታግዞ በኑባ አባላት ላይ ጥቃት ማድረሱን አስታውቆ እንደነበር አይዘነጋም።
ካለፈው አርብ ጀምሮ በሚሴሪያ እና በኑባ ጎሳዎች መካከል በአብደልአዚዝ ኤል ሂሉ በሚመራው አካባቢ በምትገኘው በላግዋ ከተማ በተፈጠረው የመሬት ውዝግብ ምክንያት ግጭት መቀስቀሱም የሚታወቅ ነው፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምት መሰረት እስከ ማክሰኞ ድረስ በጦርነቱ ወደ 12 የሚጠጉ ሰዎች ሲሞቱ 20 ቆስለዋል ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ቃጠሎውንና ዘረፋውን ሸሽተው ተፈናቅለዋል፡፡
የወቅቱ ግጭቶች እንደፈረንጆቹ በ2019 በቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር የስልጣን ዘመን በሱዳን ባለስልጣናት መካከል የትጥቅ ስምምነት ከተፈራረመ በኋላ የተከሰቱ አስከፊ የሚባሉ ግጭቶች እንደሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሱዳን እየተስተዋለ የመጣው ጎሳ ግጭት ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ኪሳራ ከማስከተሉም ለዴሞክራሲያዊ ሽግግርና ለሰላም ሂደቱ አንዱ ጠንቅ እንደሆነ ይነገራል።
በርካቶችም የጎሳ ግጭት ሱዳን የምትታመምበት መቅሰፍት ነው ሲሉ ይደመጣሉ፡፡