መስታወት የሆነው ህንጻ የአደጋ ምክንያት እስካሁን አልታወቀም
በሱዳን ጦርና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ በዋና ከተማይቱ ካርቱም ከተካሄደ በኋላ ህንጻዎች በእሳት ተያይዘዋል።
- የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ካርቱምን ዋና ከተማው አድርጎ መንግስት እመሰርታለሁ ሲል ዛተ
- ሱዳን የመከፋፈል አደጋ ተጋርጦባታል ሲል የፖለቲካ ፖርቲዎች ጥምረት አስጠነቀቀ
እሁድ እለት በማህበራዊ የትስስር ገጾች የተለቀቁ ምስሎች የታዋቂው ናይል ፔትሮሊየም ኩባንያ ህንጻ በእሳት ሲቀጣጠል አሳይተዋል።
በናይል ወንዝ አቅራቢያ የሚገኘው ባለ 18 ወለል ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ለካርቱም መለያ ምልክቷ ነበር ተብሏል።
ሾጣጣ የጣሳ ቅርጽ የያዘውና መስታወት የሆነው ህንጻ በእሳት ለመያያዙ ምክንያቱ እስካሁን አልታወቀም።
እስካሁን ድረስ በአደጋው ሞትም ሆነ ጉዳት ሪፖርት እንዳልተደረገ ቢቢሲ ዘግቧል።
የሱዳን ጦርነት ከተጀመረ ከሚያዚያ ወር ወዲህ በካርቱም የአየር ድብደባዎችና የምድር ጦርነቶች ተፋፍሞ ቀጥሏል።
ወራትን በዘለቀው የሱዳን ጦርነት የመንግስታቱ ድርጅት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሀገሪቱን ለቀው ተሰደዋል ብሏል።