ሱዳን የመከፋፈል አደጋ ተጋርጦባታል ሲል የፖለቲካ ፖርቲዎች ጥምረት አስጠነቀቀ
አጋር በነበሩት ጀነራል አልቡርሃን እና ጀነራል ደጋሎ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት አምስት ወራትን አስቆጥሯል
ኤፍሲሲ ባወጣው መግለጫ በሁለቱም አካላት መንግስት እመሰርታለሁ የሚለው ዛቻ "ሀገሪቱን የሚያፈራርስ እና የሚከፋፍል እጅግ አደገኛ ጉዳይ" ነው ብሏል
የሱዳን ዋና የተቃዋሚ ፖርቲዎች ጥምረት ተፋላሚ ኃይሎቹ ተወዳዳሪ መንግስት የሚመሰርቱ ከሆነ ሀገሪቱ ልትከፋፈል ልትከፋፈል እና ወደ ተራዘመ የእርስበእርስ ጦርነት ልታመራ እንደምትችል አስጠንቅቋል።
በፎስስ ፎር ፍሪደም ኤንዴ ቸንጅ (FFC) ይህን መግለጫ ያወጣው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ በተቆጣጠሯቸው ቦታዎች መንግስት እመሰርታለሁ የሚል ዛቻ ማሰማታቸውን ተከትሎ ነው።
ኤፍሲሲ ባወጣው መግለጫ በሁለቱም አካላት መንግስት እመሰርታለሁ የሚለው ዛቻ "ሀገሪቱን የሚያፈራርስ እና የሚከፋፍል እጅግ አደገኛ ጉዳይ" ነው ብሏል።
ጥምረቱ ሀገሪቱንም ወደለየለት የእርስበእርስ ጦርነት ያስገባታል ሲልም አስጠንቅቋል።
ባለፈው ሚያዝያ ወር በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና በሱዳን ጦር መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከዋና ከተማዋ ካርቱም የተወሰኑ ቦታዎችን እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ሱዳን ያሉ ቦታዎችን ተቆጣጥሯል። ከሱዳን ጦር ጋር በቅርቡ የተጋጨው ኤስፒኤልኤም- ኤን ደግሞ ቡድን አብዛኛውን የደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ይዟል።
የሱዳን ጦር የምስራቋን የቀይ ባህር ወደብን ጨምሮ ሌላውን የሀገሪቱን ክፍል ተቆጣጥሮ ይገኛል።
አጋር በነበሩት ጀነራል አልቡርሃን እና ጀነራል ደጋሎ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት አምስት ወራትን አስቆጥሯል።
በጦርነቱ እስካሁን አራት ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው ሲፈናቀሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከሀገራቸው ተሰድደዋል።