አቃቤ ህግ የሱዳንን ሉአላዊ ምክርቤት ፕሬዘዳንት አልቡርሀንን አልከስም አለ
አቃቤ ህግ የሱዳንን ሉአላዊ ምክርቤት ፕሬዘዳንት አልቡርሀንን አልከስም አለ
የሱዳን አቃቤ ህግ ሌትናንት ጄነራል አብደል ፋታህ አልቡርሀን ከኔታኒያሁ ጋር በመገናኘታቸው ምክንያት እንዲከሰሱ የቀረበውን ጥያቄ አለመቀበሉን አናዶሉ አረብኛ ዘግቧል፡፡
አቃቤህጉ ውድቅ ያደረገው፣ የሱዳን ሉአላዊ ምክርቤት ፕሬዘዳንት የሆኑትን ሌትናንት ጄነራል አብደል ፋታህ አልቡርሀን በእስራኤል ላይ ተጥሎ የነበረውን ማእቀብ በመጣስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኒታኒያሁ ጋር ተገናኝተዋል በሚል ከህግ ባለሙያዎች የቀረበባቸውን ክስ ነው፡፡
ለክሱ መልስ የሰጡት የ“ሰሜን ካርቱም አቃቤ ህግ” አህመድ አልኑር የህገመንገስቱ ድንጋጌ ለሉአላዊ ምክርቤት አባለትና ለሚኒስትሮች ያለመከሰስ መብት ይሰጣል ብለዋል፡፡
ነገርግን አልአትሳም የህግ ባለሙያዎችንና የአማካሪዎች ድርጀት የአቃቤ ህጉን ዉሳኔ እንደሚቀበልና አቤቱታም እንደሚያሰማ ገልጿል፡፡