ተፋላሚ ኃይሎቹ ተኩስ እንዲያቆሙ በአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ የተደረገው ጥረት ውጤት አላመጣም
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሚቲ የኢድ-አልአድሃ ወይም አረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተናጠል ተኩስ አቁም እንደሚያውጁ አስታውቀዋል።
ሄሜቲ በድምጽ ባስተላለፉት መልእክት ያወጁት ተኩስ አቁም ዛሬ እና ነገ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል።
የሱዳን ጦር በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
ተፋላሚ ኃይሎቹ ተኩስ እንዲያቆሙ በአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ የተደረገው ጥረት ውጤት አላመጣም።
ካርቱምን ጨምሮ በትላልቅ ከተሞች የሚያደርጉት ጦርነት እንቀጠለ ነው።
አሜሪካ በጂዳ ካሉት የሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ጋር በተለይም የሰብአዊ አገልግሎት አቅርቦት ማመቻቸትን በሚመለከት እየተነጋገረች መሆኗን ገልጻ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ በሱዳን ያለውን ጦርነት የማባባስ ሚና አላቸው ያለቻቸውን ሁለቱንም ኃይሎች በሚደግፉ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጥላለች።
ይህ ጦርነት ሱዳንን 30 አመታት በላይ የገዙት ፕሬዝደንት አልበሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ ሊቋቋም የነበረው የሲቪል አስተዳደር አምክኗል።