ፕሬዝደንት ሩቶ በሱዳን ያለው ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል
የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ፣በሱዳን የዘር ማጥፋት ምልክቶቾ መኖራቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዝደንት ሩቶ ለፍራንስ 24 እንደተናገሩት በሱዳን ያለው ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።
ኘሬዝደንት ሩቶ "በሱዳን እየተካሄደ ያለው ነገር ተቀባይነት የለውም። ወታደራዊ ኃይል በሁለቱም ወገን ሀገሪቱን ለማውደም እና ንጹሃንን ለመግደል ጥቅም ላይ ውሏል። ይህ ጦርነት ትርጉም የለውም፤ በምንም መንገድ ትክክለኛ አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ሩቶ የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም ያለመ ቀጣናዊ ስብሰባ አድርገው ነበር።
መፍትሄ የሚገኘው ጀነራል አል ቡርሃንን እና ጀነራል ሄሜቲን ማግኘት ሲቻል መሆኑን የገለጹት ኘሬዝደንቱ ይህም እንደሚሳካ ተናገረዋል።
በሱዳን በአንድ ወቅት አጋር በነበሩት በሱዳን ጦር በመሪ አል ቡርሃን እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይልን በሚመሩት ጀነራል ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ የተጀመረው ጦርነት ስስተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል።
ሁለቱ ተፋለሚዎች በተያየ ጊዜ ተኩስ ለማቆም ቢስማሙም፣ እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም። ጦርነቱ ቀጥሏል።