የሱዳን ወታደራዊ መንግስት የቀድሞውን ፋይናንስ ሚኒስትር ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሊሾም መሆኑ ተሰማ
የጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን መልቀቅ ሱዳናውያንን አወዛግቧል
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በዛሬው እለት ስልጣን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል
የሱዳን ሉአላዊ ወታደራዊ የሽግግር መንግስት የቀድሞውን የፋይናንስ ሚኒስትር ኢብራሂም አል ባደዊ በዛሬው እለት ከስልጣን የለቀቁትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን በመተካት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንደሚሾሙ ምንጮች ለአል ዐይን ኒውስ ገልጸዋል፡፡
የሉዓላዊው ምክር ቤት ኃላፊ ሌተና ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የሃምዶክን ተተኪነት በተመለከተ ከኤል ባዳውይ ጋር ይፋዊ ግንኙነት ማድረጋቸውን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡ ኤል ባዳውይ “ለመጽደቅ ወይም ውድቅ ለማድረግ ከቅርብ ሰዎች ጋር እየተመካከረ ነው።
የ68 አመቱ ኢብራሂም አል ባዳዊ በሃምዶክ የመጀመሪያ መንግስት በፈረንጆቹ እስከ ሀምሌ 2020 ድረስ የገንዘብ ሚኒስትርነት አገልልዋል፡፡ ኢብራሂም አል ባዳዊ በአለም ባንክን ጨምሮ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ባለሙያ ሆነው ሰርተዋል፡፡
አል-ባዳዊ በታህሳስ 2019 ያቀረበውን በጀት ካስቀመጠው ሃምዶክ ጋር አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ በ2020 ስራቸውን መልቃቸው ይታወሳል፡፡
ባለፈው ታህሳስ ወር ከአልሱዳኒ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በሰጡት መግለጫ፣ “የምንዛሪ ተመንን ማስተካከል እና ሌሎች ቀይ መስመሮች እንደሆኑ ተነግሮኝ ነበር፣ እና እኔ አልኳቸው፣ እሺ፣ ፕሮግራማችሁን የሚተገበር ሚኒስትር ፈልጉ" ብለው መናገራቸውን ገልጸዋል፡፡
አል-ባዳዊ ከመንግስት ስራ ስለወጡበት የተሰማቸውን ተናግረዋል፤ "አንድ ሴራ እንዳለ ይሰማኛል ፣ ግን በእርግጠኝነት መናገር አልችልም” ማለታቸው ይታወሳል፡፡
አል ባዳዊ በ1978 ከካርቱም ዩኒቨርስቲ ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ የተመረቀ ሲሆን በሰሜን ካሮላይና የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ በስታስቲክስ ሁለተኛ ዲግሪ ያገኘ ሲሆን ከዛው ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ እና ስታቲስቲክስ የዶክትሬት ዲግሪ አግኝቷል።
በፈረንጆቹ በ2005 በተፈረመው የሱዳን የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ ውስጥ በሱዳን በተካሄደው የመልሶ ግንባታ ፕሮግራም የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ የማስተባበር ስራ ሰርተዋል፡፡በዱባይ ኢኮኖሚክ ካውንስል የኢኮኖሚ ፖሊሲና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል።
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ “ከስልጣናቸው የለቀቁት ከሀገሪቱ ጦር ጋር የተካሄደውን የአጭር ጊዜ የፖለቲካ ስምምነት በማብቃቱ”መሆኑ በምክንያትነት አቅርቧል፡፡
"ሀገራችን ወደ አደጋ እንዳትገባ የምችለውን ያህል ሞከርኩ፤ አሁን ግን ከጠቅላይ ሚኒስትርነቴ በመልቀቅ ለሌላ የዚህች ክቡር ሀገር ወንድ ወይም ሴት እድል ለመስጠት ወሰንኩ"ም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ፡፡