በሱዳን በርካታ ዝጎች የተሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው
ወደ ካርቱም ከተማ የሚያስገቡ ድልድዮችም በሀገሪቱ የፀጥታ አካላት እንዲዘጉ ተደርጎ ነበረ
የሱዳን መንግስት ከሰልፉ ቀደም ብሎ በመላ ሀገሪቱ የኢንተርኔት እና የሞባይል ስልክ አገልግሎት አቋርጧል
በሱዳን እየተካሄደ ካለው ሰልፍ አስቀድሞ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ እንዲዘጋ መደረጉ እየተገለጸ።
በሀገሪቱ በተደጋጋሚ ሲካሄድ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ሲሆን ይህንን ተከትሎም የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በዋና ከተማዋ በድጋሚ እንዲዘጋ ተደርጓል ነው የተባለው።
የዛሬው ሰልፍ ዓላማ በቅርቡ በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች በጸጥታ ሃይሎች የተገደሉትን ለማሰብ እና ጥቅምት ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት ለመጠየቅ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሞባይል ኢንተርኔት የተቋረጠ ሲሆን ፤ የፀጥታ ኃይሎች ካርቱምን ከባህሪ እና ከኦምዱርማን የሚያገናኙ ድልድዮችን ዘግተዋል ተብሏል።
ከቀናት በፊት ተካሂዶ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በኦምዱርማን ከተማ ብቻ ስድስት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተሰምቷል። የ
ሱዳን ሀኪሞች ማህበር በሀገሪቱ ተቃውሞ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ50 መብለጡን ገልጿል።
በርካታ ሱዳናውያን ወደ ስራ ለመሄድ አስበው የነበረ ሲሆን፤ የብሉ ናይል ድልድይ መዘጋት እንዳስገረማቸው በካርቱም የሚገኘው የአል ዐይን ዘጋቢ ተመልክቷል። በድልድዩ መዘጋት ምክንያት በርካታ መኪኖች መቆማቸውንም ዘጋቢው ተመልክቷል።
የናይል ድልድይ ዋና ከተማዋን ካርቱምን ከሱዳን ዋና ከተማ በስተሰሜን የምትገኘውን የኢንዱስትሪ ከተማ ባህሪን የሚያገናኝ ሲሆን ሰራተኞቹ ወደ ስራ ቦታቸው የሚሄዱበት ብቸኛ ድልድይ ነበር።
የሱዳን ባለስልጣናት በዋና ከተማይቱ ካርቱም የሚገኙ ሌሎች ድልድዮችን ያዘጉት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ሰልፍ ወደ ፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግስት እንዳያመራ ለማድረግ እንደሆነም ነው የተገለጸው።
በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ የምትገኘው ሱዳን ተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፎች እየተደረጉባት ሲሆን የሽግግር መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የሥልጣን መልቀቂያ ያስገባሉ ሲባል ነበር።