የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ም/ ቤት በተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተከሰተውን ሁከት አወገዘ
ምክር ቤቱ በህገወጥ ሰልፈኞች ላይ ወታደራዊ እርምጃዎች እንዲወሱ የጸጥታ ኃይሎች አዝዣለሁ ብሏል
የሱዳን መሪዎች አለመግባባት ሀገሪቱን ወደ ማያስፈልግ ብጥብጥ እንዳይወስዳት ተሰግቷል
የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ባለፈው ሃሙስ በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ለአራት ተቃዋሚዎችን ሞት እና በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሌሎች መቁሰል ምክንያት የሆነውን ሁከት አወገዘ።
ምክር ቤቱ የሚመለከታቸው አካላት ባወጣው መግለጫ መሰል ድርጊቶች እንዳይደገሙ ህጋዊ እና ወታደራዊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንዲሁም ማንኛውም አጥፊ ከቅጣት እንዳያመልጥ ማዘዙንም አስታውቋል።
የሱዳን ፖሊስ "በኦምዱርማን አራት ተቃዋሚዎች ሲገደሉ 297 ሌሎች 49 ፖሊሶች የሚገኙባቸው ሰዎች ቆስለዋል" ማለቱ አይዘነጋም፡፡
ሃሙስ እለት በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍአንዳንድ ሰልፈኞችን ከሰልፉ አላማ ውጭ የሆኑ መልእክቶች ሲያንጸባርቁ እና በፖሊስ ሃይሎች ላይ ጥቃት ሲያደርሱ ነበር በማለት፤ የሱዳን ፖሊስ እንደከሰሰም እንዲሁ የሚታወስ ነው።
በሱዳን ከሁለት ወር በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሚመራው የሲቪል አስተዳድር ላይ መፈንቅለ መንግስት መፈጸሙን ተከትሎ ነበር ሱዳን ወደ ባሰ አለመረጋጋት የገባችው፡፡
በጀነራል አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦርም ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ላይ አርምጃ በመውሰድ ላይ ሲሆን እስካሁን ድረስ 54 ሰላማዊ ሰልፈኞች በሱዳን ጦር በተተኮ ጥይት መገደላቸውን የሀገሪቱ ሀኪሞች ማህበር መረጃ ያመለክታል፡፡
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የሱዳን ጦር ሙሉ ለሙሉ ከስልጣን እስኪወገድ ድረስ ተቃውሟቸውን እንደማያቆሙ በመግለጽ ላይ ሲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላ ሀምዶክ ክህደት እንደፈጸሙባቸውም በመናገር ላይ ናቸው፡፡
ሃሙስ እለት የወታደራዊ መንግስት ተቃዋሚዎች አዲስ ህዝባዊ ተቃውሞ ያሰጋቸው የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች የካርቱም ከተማ ጎዳናዎችና መንገዶች ተስተውሏል፡፡
የሱዳን ጦር፣ ፖሊሶች እና ፓራሚሊተራዊ ጥበቃዎች በካርቱምን ጎዳናዎች በከፍተኛ ቁጥር ተሰማርተው ፣የመርከብ ኮንቴይነሮች ዋና ከተማዋን ከሰሜን አቅጣጫ ከመንታ ከተማዋ ኦምዱርማን ጋር የሚያገናኘውን የናይል ድልድይ ቢዘጉም ፤ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ግን ወደ አደባባይ ከመውጣት አላገዳቸውም ነበር፡፡
የገለልተኛ ዶክተሮች ኮሚቴ እንደገለጸው፤ የዲሞክራሲ ደጋፊና ማህበረሰብ አንቂዎች በሰራዊቱ ጥቅምት 25 የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም የጎዳና ላይ የሚያደርጉዋቸውን ሰልፎችን እንደቀጠሉ ናቸው።
በሱዳን መሪዎች መካከል ያጋጠመውን የፖለቲካ ፍጥጫ ተከትሎ አሁን ላይ በሱዳን የሚሰራ መደበኛ መንግስት አለ ለማለት እንደማይቻል በረካቶች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡