ህዝባዊ ተቃውሞ ያሰጋቸው የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች ወደ ካርቱም የሚያስገቡ መንገዶችን ዘጉ
በካርቱም ዋና ዋና መንገዶች ላይ “አዳዲስ የስለላ ካሜራዎች ተገጥሟል” ተብሏል
የሱዳን መሪዎች የፖለቲካ ፍጥጫ ሀገሪቱ “መደበኛ መንግስት እንዳይኖራት እስከማድረግ” ደርሷል
የወታደራዊ መንግስት ተቃዋሚዎች አዲስ ህዝባዊ ተቃውሞ ያሰጋቸው የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች የካርቱም ከተማ ጎዳናዎችና መንገዶች ዘግተዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የሱዳን ጦር፣ ፖሊሶች እና ፓራሚሊተራዊ ጥበቃዎች በካርቱምን ጎዳናዎች በከፍተኛ ቁጥር መሰማራታቸው እንዲሁም ፣የመርከብ ኮንቴይነሮች ዋና ከተማዋን ከሰሜን አቅጣጫ ከመንታ ከተማዋ ኦምዱርማን ጋር የሚያገናኘውን የናይል ድልድይ መዘጋቱ የፈረንሳዩ የዜና ወኪል /ኤ.ኤፍ.ፒ/ ዘግቧል፡፡
ድልድዮቹ የተዘጉት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወደ ጎዳናዎች በወጡበት በታህሳስ 26ቱ የመጨረሻ ተቃውሞ የነበረ ቢሆነም ዛሬ ለታቀዱት የተቃውሞ ሰልፎች፣በዋና ዋና መንገዶች ላይ አዳዲስ የስለላ ካሜራዎች መገጠማቸውም ታውቋል።
የገለልተኛ ዶክተሮች ኮሚቴ እንደገለጸው፤ የዲሞክራሲ ደጋፊና ማህበረሰብ አንቂዎች በሰራዊቱ ጥቅምት 25 የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም የጎዳና ላይ የሚያደርጉዋቸውን ሰልፎችን እንደቀጠሉ ናቸው።
በሱዳን የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ በህዳር ወር ላይ ከሲቪል ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር አወዛጋቢ ስምምነት ያደረገው መንግስት፤የህዝብን ፍላጎት በመረዳት የህዝብን ቁጣ በማብረድ በኩል ኃላፊነቱ እንዲወጣ ጠይቋል፡፡
ኤምባሲው “በሰላማዊ መንገድ የዲሞክራሲ ፍላጎትን እና የመናገርን ነጻነት የሚለማመዱ ግለሰቦችን ማክበር እና መጠበቅ እንደሚያስፈልግና ለዚህም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሚያደርግ”ም ገልጿል።
"ኃይልን በመጠቀም ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ እንጠይቃለን እናም ባለስልጣናት በዘፈቀደ እስራት ከመቅጠር እንዲቆጠቡ እናሳስባለን"ም ብሏል ኤምባሲው፡፡
ታህሳስ 19 በተካሄደው ተቃውሞ ቢያነስ 13 ሴቶች መደፈራቸው ተመድ መግለጹ የሚታወስ ነው፡
በሱዳን መሪዎች መካከል ያጋጠመውን የፖለቲካ ፍጥጫ ተከትሎ አሁን ላይ በሱዳን የሚሰራ መደበኛ መንግስት አለ ለማለት እንደማይቻል ይገለጻል፡፡