በአየር ንብረት ለውጥ ድርድር የሌለው የሙቀት መጨመርን መቀነስ ነው- ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር
የአፍሪካ ተስፋዎች በአረብ ኤምሬቶች የኮፕ 28 ጉባኤ ላይ የተጣበቀ ነው ተባለ
የፓሪስ ስምምነት ፈራሚዎች የተጣራ ዜሮ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን በ2050 ለመድረስ ቃል ገብተዋል
የዓለም ሙቀት መጨመርን ወደ 1.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የመገደብ ትልም ልቀትን ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ዘመቻዎችን ለሚመሩ ብዙ ሀገራት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም።
የአረብ ኤምሬትስ የኢንደስትሪና የላቀ ቴክኖሎጂ ሚንስትር እንዲሁም የኮፕ28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር የሙቀት መጨመርን ለመገደብ የተያዘው 1.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ግብ መተው የለባትም ብለዋል።
በመጪው ህዳር በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከሚካሄደው 28ኛው የዓለም መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ ምክክር ቀደም ብሎ አል ጃበር ዓለም አቀፍ ጉብኝት በማድረግ የ2015ን የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት ግቦችን ማሳካት አስፈላጊ መሆኑን ደጋግመው አሳስበዋል።
- የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃን ማፋጠን ለኢንቨስትመንትና ዘላቂ እድገት እድል ይፈጥራል- የኮፕ-28 ፕሬዝዳንት
- አረብ ኢሚሬትስ ለአየር ንብረት ለውጥ የሚደረገው ጥረት በእጥፍ እንዲያድግ ጠየቀች
በ195 ሀገራት የተፈረመው ስምምነቱ ከቅድመ-ኢንዱስትሪ ጊዜ ጀምሮ በአማካይ የዓለም ሙቀት መጨመርን ከ2 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች በማድረግ እና በ1.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ለመገደብ ተሞክሯል።
የሴኔጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአል ዐይን ኒውስ የአፍሪካ አህጉር ተስፋዎች በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኮፕ 28 ጉባኤ ላይ የተጣበቀ ነው ብለዋል።
የፓሪስ ፈራሚዎች የተጣራ ዜሮ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን በ2050 ለመድረስ ቃል ገብተዋል። 2019ን እንደ መነሻ በመጠቀም በ2030 የ43 በመቶ ቅነሳን ያካትታል።
የፓሪስ ስምምነት ከተፈረመ ከሰባት ዓመት በኋላ 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ግብ በጥልቀት መፈተሽ አለበት የሚል ጫና በርትቶበታል።
አንዳንድ የአየር ንብረት ተመራማሪዎች ግቡን ማሳካት ከአሁን በኋላ አይቻልም ብለው ሲያምኑ ሌሎች ደግሞ ጠንካራ እርምጃዎች ከተወሰዱ ወደ ትክክለኛው መንገድ መመለስ ይቻላል ብለው ይሞግታሉ።
በወሩ መጨረሻ የአየር ንብረት ፓናል የ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ግብን በሚመለከት ሪፖርቱን ይፋ ያደርጋል።