ጎግል የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የተጀመረውን ጥረት በማገዝ ላይ መሆኑ ተገለጸ
ብሎክ ቼይን በተሰኘው ቴክኖሎጂ አማካኝነት የአቪዬሽን ተቋማት ለታዳሽ ሀይል ትኩረት እንዲሰጡ በመደገፍ ላይ ነው ተብሏል
አውሮፕላኖች ወደ ካበቢ አየር ከሚለቀቁ በካይ ጋዝ መጠን ውስጥ የ90 በመቶ ድርሻ አላቸው
ጎግል የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የተጀመረውን ጥረት በማገዝ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት ዘላቂ የአቪየሽን ነዳጅ ወይም በምህጻረ ቃሉ ዛፍ የተሰኘ ፕሮግራም ለዓለም ይፋ ተደርጓል፡፡
ይህ ፕሮግራም አውሮፕላኖች ለሀይል ምንጭነት በሚጠቀሟቸው ነዳጅ ምክንያት በመተው ለታዳሽ ሀይል ትኩረት እንዲሰጡ ለማድረግ ያለመ ነው።
በዓለማችን ወደ ከባቢ አየር ከሚለቀቁ በካይ ጋዝ መጠን ውስጥ አውሮፕላኖች የ90 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ።
በዚህ ጥናት መሰረት አውሮፕላኖች እና ጄቶች የሚጠቀሙትን የነዳጅ ሀል እንዲቀንሱ አልያም ወደ ታዳሽ ሀይል አማራጭ እንዲመጡ ለማድረግ ያለው ይህ ዛፍ የተሰኘው ፕሮግራም በጎግል እየተደገፈ ተብሏል።
በጎግል ብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ የሚደገፈው ይህ ፕሮግራም አገልግሎት ሰጥተው ከተጣሉ ተረፈ ምርቶችን ዳግም በመጠቀም ወይም ከባዮ ፊዩል ሀይል እንዲያመርቱ ማድረግን ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
የአየር ንብረት ለውጥ ዘላቂ የልማትን እያደናቀፈ እንደሆነ ተገለጸ
አዲሱ የጎግል የታዳሽ ሀይል ፕሮግራም በአሜሪካ ቢዝነስ ትራቭል እና ሼል አቪዬሽን ተቋም ክትትል እና ቁጥጥር እየተደረገበት ነው ተብሏል።
ፕሮግራሙን ከጎግል በተጨማሪም የአሜሪካ ባንኮች፣ አየር መንገ፵፣ ጄት ብሉ እና ጃፓን አየር መንገዶችም አብረው በመስራት ላይ እንደሆኑ ተገጿ ል።
በዚህ ፕሮግራም መሰረት እስከ 15 ሺህ በረራዎችን ማካሄድ የሚያስችል ታዳሽ ሀይል ለማመንጨት እቅድ ተይዟል ተብሏል።
በጎግል እና በሌሎች የአሜሪካ ኩባንያዎች እየተሞከረ ያለው የሀይል ልማት ፕሮግራም ከአውሮፕላኖች ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የበካይ ጋዝ መጠን በ80 በመቶ የመቀነስ አቅም ይኖረዋልም ተብሏል።