ታዋቂው የእግር ኳስ አሰልጣኝ ኤሪክሰን በህይወት የመቆየት እድሉ ለወራት ብቻ እንደሆነ ተናገረ
የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኤሪክሰን በጣፊ ካንሰር መጠቃታቸውን ይፋ አድርገዋል
የካንሰሩ ሁኔታ የመጨረሻ ደረጃ ላይ መሆኑን ያወቁት ዘግይተው እንደሆነም ኤሪክሰን ተናግረዋል
ታዋቂው የእግር ኳስ አሰልጣኝ ኤሪክሰን በህይወት የመቆየት እድሉ ለወራት ብቻ እንደሆነ ተናገረ፡፡
በርካታ የእግር ኳስ ክለቦችን እና ብሔራዊ ቡድኖችን በማሰልጠን የሚታወቁት ስቨን ጎራን ኤሪክሰን በጣፊያ ካንሰር መጠቃታቸውን ለህዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡
የቀድሞ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ያሰለጠኑት ስዊድናዊው ኤሪክሰን ባጋጠማቸው የካንሰር ህመም ምክንያት ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ በህይወት እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡
ባሳለፍነው ዓመት በርካታ ዝግጅቶችን እና ፕሮግራሞችን በጠየና ምክንያት መገኘት አልቻልኩም ነበር፣ ሁሉም ሰው የሆነ ከባድ ህመም እንዳለብኝ ያውቅ ነበር ሲሉም ለስዊድን ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡
በጣፊያ ካንሰር እንደተጠቃሁ ያወቅሁት ተዝለፍልፌ ከወደቅሁ እና ወደ ህክምና ቦታ ከወሰዱኝ በኋላ ነው የሚሉት አሰልጣኝ ኤሪክሰን የበሽታው ደረጃ ሊታከም የማይችል እንደሆነም ይፋ አድርገዋል፡፡
የ75 ዓመቱ አሰልጣኝ ኤሪክሰን አክለውም በህይወት የምቆየው ቢበዛ አንድ ዓመት ነው ያሉ ሲሆን እውነታውን መቀበል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
አሰልጣኙ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በተጨማሪም የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ፣ ጣልያኑን ላዚዮ፣ ከፖርቹጋሉ ቤነፊካ እንዲሁም ከስዊድኑ ጎተንበርግ ክለቦችን አሰልጥነው ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችለዋል፡፡
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ለአሰልጣኝ ኤሪክሰን ፍቅር እና አክብሮት እንዳለው በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ መልዕክት አስፍሯል፡፡