ስፖርት
አርጀንቲና ፊፋ በቅርቡ ባወጣው የእግር ኳስ ደረጃ 1ኛነቷን አሰጠበቀች
ባለፈው ሳምንት በወዳጅነት ጨዋታ በጀርመን የተሸነፈችው ፈረንሳይ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች
አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ደረጃዋን በማሻሻል ወደ 13ኛ ከፍ ብላለች
የዓለም እግር ኳስ ፌደሬሽን ፊፋ በቅርቡ ባወጣው የእግርኳስ ደረጃ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ አርጀንቲና አንደኛ ደረጃዋን አስጠብቃለች።
ባለፈው ሚያዝያ ወር ብራዚልን ከዙፏና በማውረድ አንደኛ የሆነችው አርጀንቲና በፈረንጆቹ 2026 ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢኳዶር እና ቦልቪያን ካሸነፈች በኋላ አንደኛነቷን ማስቀጠል ችላለች።
ባለፈው ሳምንት በወዳጅነት ጨዋታ በጀርመን የተሸነፈችው ፈረንሳይ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ብራዚል፣ እንግሊዝ፣ ቤልጀየም እንደቅደምተከተላቸው ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
በዚሁ የፊፋ ደረጃ ፖርቱጋል ደረጇዋን በማሻሻል ከአንድ እስከ አስር ውስጥ ስትካተት ጣሊያን በአንጻሩ አንድ ደረጃ በመቀነስ ዘጠንኛ ላይ ትገኛለች።
አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ደረጃዋን በማሻሻል ወደ 13ኛ ጀረጃ ከፍ ብላለች።
ቀዳሚ 10 ሀገራት በደረጃ
1.አርጀንቲና
2. ፈረንሳይ
3. ብራዚል
4. እንግሊዝ
5. ቤልጄም
6. ክሮሺያ
7. ኔዘርላንድ
8. ፖርቹጋል
9. ጣሊያን
10. ስፔን